banner

ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ምን አጋጠመው?

​#FastMereja I ከለንደን ወደ አዲስ አበባ የተመለሰው ታዋቂው ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ «ታምሜ ገባሁ» ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አድናቂዎቹን ስጋት ውስጥ ጥሎ የነበረ ቢሆንም አደጋው አሳሳቢ እንዳልሆነ ታውቋል።

​ድምጻዊው ከለንደን ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ላይ ሳለ በአየር መንገድ ውስጥ እርጥበት የነካው ሴራሚክ አዳልጦት የወደቀ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ጉዳዩን በተመለከተ ወደ ድምጻዊው ያቀናው ጋዜጠኛ ሰይፉ ፋንታሁን ከጎሳዬ ጋር በመሆን በሰጠው ማብራሪያ፣ ያጋጠመው ክስተት ከፍተኛ የሚባል የጤና አደጋ እንዳልሆነና አድናቂዎቹ ስጋት እንዳይገባቸው መልዕክት አስተላልፏል።

Leave a Comment