banner

በላስታ ላሊበላ ለቀናት የተካሄደውን ምህላ ተከተሎ ዝናብ መጣሉ ተገለጸ

#FastMereja I በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ላሊበላና አካባቢው የክረምቱ ዝናብ ዘግይቶ በነበረበት ወቅት ለሰባት ቀናት የተካሄደውን ሃይማኖታዊ የምህላ ጸሎት ተከተሎ ወቅቱን የጠበቀ ዝናብ መጣል መጀመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታወቁ።

በሰሜን ወሎ ዞን በላስታ ላሊበላና በዙሪያው በሚገኙ አካባቢዎች የዘንድሮው የክረምት ዝናብ በመዘግየቱ ምክንያት ገበሬው ዘሩን በደረቁ ዘርቶ ከፍተኛ የስጋትና የጭንቀት ሁኔታ ውስጥ ወድቆ እንደነበር ተገልጿል። የአካባቢው ማህበረሰብና የገዳሙ አባቶች ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲወራረድ የመጣውን ባህላዊና ሃይማኖታዊ ስርዓት በመከተል ቤተ ሚካኤል (ጎልጎታ) ተሰብስበው ላለፉት ሰባት ቀናት አበይት የምህላ ጸሎት ሲያደርሱ ቆይተዋል።

በቅዱስ ላሊበላ ገዳም አባቶች ዘንድ በየዓመቱ በታኅሣሥ፣ በሰኔ እና በመስከረም ወራት የሚደረጉ የተለመዱ የምህላ ጸሎቶች እንዳሉ የሚታወቅ ሲሆን፣ የዘንድሮውን የዝናብ መዘግየት ተከተሎ የተደረገው የጸሎት ሥነ-ሥርዓት በስድስተኛው ቀን የዝናብ ምልክት ማሳየቱንና በሰባተኛው ቀን ደግሞ ምድሪቱን የሚያርስርቅ ዝናብ መጣሉ ተመልክቷል። ይህም በስጋት ውስጥ የነበረውን የአካባቢውን አርሶ አደርና አጠቃላይ የማህበረሰብ ክፍል ከፍተኛ ተስፋ ያሰነቀ አጋጣሚ ሆኗል።

Leave a Comment