0
#FastMereja I የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ያለፈባቸውን የታሪክ ውጣ ውረዶች እና ተቋማዊ የለውጥ ጉዞ የሚያስነብብ «ጽናት፡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ታሪካዊ የለውጥ ጉዞ» የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር የመሰብሰቢያ አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ እንደሚመረቅ ተገለጸ።
መጽሐፉ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት በዶክተር አሥራት ዓፀደወይን የተጻፈ ሲሆን፣ ተቋሙ በረጅም ዘመን ጉዞው ያሳለፋቸውን ፈተናዎች፣ ያመጣቸውን ተቋማዊ ለውጦች እና ያስመዘገባቸውን ስኬቶች በሰፊው የሚዳስስ ታሪካዊ ሰነድ እንደሆነ ታውቋል።
በዕለቱ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በሚካሄደው የይፋዊ ምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ ጥሪ የተደረገላቸው ልዩ ልዩ እንግዶች፣ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት እንደሚታደሙ ከተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
