📌 ኢትዮጵያ የ2027ቱን አህጉራዊ ፌስቲቫል እንድታዘጋጅ ተወሰነ
#FastMereja I የኢትዮጵያ ሼፎች ማህበር ፕሬዝዳንት ። በደቡብ አፍሪካ እና በስዋቲኒ በተካሄደው የ2026 የአፍሪካ ሼፎች ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የተሳተፉት ሼፍ ሄኖክ ይህን ከፍተኛ ኃላፊነት ከመጨበጣቸውም በላይ፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ የ2027ቱን የመላው አፍሪካ የሼፎች ፌስቲቫል በጋራ እንድታዘጋጅ ውሳኔ ተላላፏል።
በደቡብ አፍሪካ እና በስዋቲኒ አስተናጋጅነት በተካሄደው በዚህ አህጉራዊ መድረክ የአፍሪካ የምግብ ግብአቶች፣ የአዘገጃጀት እና የአመጋገብ ታሪክ በሰፊው የተዳሰሰ ሲሆን፣ ዘርፉን የሚያጎለብቱ የተለያዩ አለም አቀፋዊ ስልጠናዎችም ተሰጥተዋል። ኢትዮጵያ እጅግ በርካታ የተፈጥሮ የምግብ ግብአቶች እና ሀብታም የአመጋገብ ባህል ያላት ሀገር እንደመሆኗ መጠን፣ ይህ ታሪካዊ አጋጣሚ ሀገሪቱ ያላትን እምቅ ሀብት ለመላው አለም ለማስተዋወቅና በገበያ ላይ በማቅረብ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንድታገኝ ትልቅ መንገድ የሚከፍት መሆኑ ተገልጿል።
ይህንን ተከትሎ ኢትዮጵያ የ2027ቱን አህጉራዊ የሼፎች ፌስቲቫል እንድታዘጋጅ መመረጧ በምግብ ቱሪዝም እና በባህል ልውውጥ ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ሲሆን፣ የሀገሪቱን ገጽታ በበጎ መልኩ በመገንባት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታመናል።



