banner

ሶማሊያ በአማራ ክልል በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለኢትዮጵያ ማጽናኛ እና ሐዘኗን ገለጸች

#FastMereja I የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በአማራ ክልል በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ።

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ አገሪቱ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም አስታውቃለች። ሚኒስቴሩ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦች እና ወዳጆች መጽናናትን የተመኘ ሲሆን፣ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ደግሞ በፍጥነት እንዲያገግሙ መልካም ምኞቱን አስተላልፏል።

በተጨማሪም በአደጋው አካባቢ የተጎዱትን ለመታደግ እና የጎደሉትን ለመፈለግ እየተደረገ ያለውን የእርዳታና የመፈለግ ስራ ያደነቀው የሶማሊያ መንግሥት፣ በጸሎት እና በሐሳብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እንደሚገኝ አረጋግጧል።

Leave a Comment