banner

በፖላንድ የአውሮፓ ትልቁ የድንግል ማርያም ሃውልት ተመረቀ

#FastMereja I በፖላንድ ማዕከላዊ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ኮኖቶፒ መንደር 55.6 ሜትር ርዝመት ያለው የአውሮፓ ትልቁ የድንግል ማርያም ሃውልት ግንባታ ተጠናቆ በይፋ ተመረቀ።

በፖላንድ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውን የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ፍልሰታ በዓል ምክንያት በማድረግ ነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ.ም (ኦገስት 15) የተመረቀው ይህ ግዙፍ መንፈሳዊ ሃውልት፣ የሀገሪቱን የረጅም ዘመን ክርስቲያናዊ ማንነት እና እምነት የሚያጎላ አዲስ ምልክት ሆኖ ተመዝግቧል።

ለ18 ወራት ያህል ሲካሄድ የቆየውን የዚህ ሃውልት ግንባታ ለማጠናቀቅ በልዩ ምህንድስና የተሰሩ ወደ 2,500 የሚጠጉ አካላት ጥቅም ላይ የዋሉ ሲሆን፣ ዋናው መሐንዲስ እንደገለጹት ከሆነ ህንፃው ያለምንም ከፍተኛ የመጠገን ስራ ከ150 እስከ 300 ዓመታት ለመቆየት በሚያስችል ጥንካሬ የተገነባ ነው።

ይህ አዲስ መንፈሳዊ ማዕከል ለፀሎት እና ለሃሳብ ማሰላሰያ የሚሆኑ ክፍሎችን፣ የከተማዋን መልካም ምድር ከፍ ብሎ ለመመልከት የሚያስችል መመልከቻ ሰገነት እና ለሁሉም አይነት ጎብኚዎች ምቹ የሆኑ መገልገያዎችን አሟልቶ ይዟል።

ለበርካታ ፖላንዳውያን ለድንግል ማርያም ያላቸው ፍቅርና እምነት ከባህላዊ እሴት በላይ የቤተሰብ፣ የሃይማኖት እና የታሪክ ህያው መገለጫ እንደሆነ የሚነገር ሲሆን፣ ይህ ሃውልትም የሀገሪቱን ክርስቲያናዊ ቅርሶች ለትውልድ አስተላልፎ ለማቆየት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተገልጿል።

Leave a Comment