#FastMereja I በኢትዮጵያ በቤት እቃዎች አቅርቦት ዘርፍ የሚታወቀው ALLIKE Furniture እና የሜሪ ዲዳ Promotion and Events መስራች፣ ታዋቂዋ የሚዲያ ባለሙያ ሜሪ ዲዳ ዲሳሳ ባለፉት ሦስት ዓመታት በጋራ ባከናወኗቸው የማስተዋወቅና የዲጂታል ይዘት ሥራዎች ያስመዘገቧቸውን ስኬቶች መሠረት በማድረግ የብራንድ አምባሳደርነት ስምምነታቸውን በይፋ ማደሳቸውን አስታወቁ።
በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው የዕድሳት ስምምነት በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን የሥራ አጋርነት፣ የጋራ ስኬትና የወደፊት ራዕይ ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑ ተገልጿል። ይህ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት የስምምነት እድሳት ብቻ ሳይሆን ALLIKE Furniture በቤቴል አካባቢ አዲስ የከፈተውን ዘመናዊ ቅርንጫፍ ለህዝብ በይፋ የአስተዋወቀበት ልዩ ሁነቶች የተከናወኑበት መሆኑ ተመልክቷል።
ALLIKE Furniture ሜሪ ዲዳን እንደ የብራንዱ ፊት አድርጎ ለመቀጠል የወሰነው በህዝብ ዘንድ ባላት ከፍተኛ ተወዳጅነት ብቻ ሳይሆን፣ በምትወክላቸው እሴቶች፣ መልካም ስነ-ምግባሯ፣ በተፅዕኖዋ እና ከማህበረሰቡ ጋር ባላት እውነተኛ ትስስር ላይ በመመስረት እንደሆነ የድርጅቱ መረጃ ያመለክታል። በመድረክ መሪነቷ፣ በተዋናይነቷ፣ በሥራ ፈጣሪነቷ፣ በቋንቋ ችሎታዋ እና በOBN እንዲሁም በYouTube በሚሰራጨው “Kaameettii Podcast” ፕሮግራሟ ሰፊ ተቀባይነት ያገኘችው ሜሪ ዲዳ፣ የድርጅቱን እሴቶችና ራዕይ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር የምታገናኝ ጠንካራ ድልድይ ሆና እንደቀጠለች ተብራርቷል።
ባለፉት ሦስት ዓመታት ሜሪ ዲዳ የብራንዱ ተወካይ በመሆን በማስተዋወቂያ ሥራዎች፣ በሚዲያ፣ በዲጂታል ይዘቶች እና በልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች ላይ በንቃት ተሳታፊ የነበረች ሲሆን፣ በቀጣይም ሁለቱ ወገኖች በፈጠራ፣ በጥራት እና በመተማመን ላይ የተመሰረቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ ይዘቶችን ለማህበረሰቡ ለማቅረብ በጋራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።




