0
#FastMereja I ኢትዮጵያዊው የዩቲዩብ ይዘት ፈጣሪ አቤል ብርሃኑ ናይጄሪያ ሌጎስ ውስጥ በተካሄደው የፓን አፍሪካን አዋርድ (PALCA 2026) መድረክ ላይ «የአመቱ የጉዞ ተፅዕኖ ፈጣሪ» (Travel Influencer of the Year) ክብርን በመጎናፀፍ ሀገሩን በድጋሚ ማስጠራቱን አስታወቀ።
በዲጂታል ይዘት ዝግጅት እና ጉዞ ዘርፍ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አፍሪካውያን የሚሰጠውን ይህን አህጉራዊ ሽልማት የተቀበለው አቤል፤ በዩቲዩብ የመረጃ መድረኩ አማካይነት የዓለምን ድንቅ ታሪኮች እና ባህሎች ለተከታታዮቹ በማቅረብ ረገድ ላሳየው ጥረት እውቅና እንደተሰጠው ገልጻል።
ተሸላሚው አቤል ብርሃኑ ሽልማቱን ከተቀበለ በኋላ ባስተላለፈው መልእክት፤ የልጅነት ህልሙ እውን እንዲሆን ላደረገው ፈጣሪ ምስጋናውን አቅርቧል። አክሎም ለዚህ የስኬት ደረጃ እንዲደርስ በስራው እና በህይወቱ ድጋፍ ለላገዙት ባለቤቱ፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለስራ አጋሮቹ እንዲሁም ስራዎቹን በየእለቱ ለሚከታተሉ የቻናሉ ቤተሰቦች ምስጋናውን ሰጥቷል።
ሽልማቱ የጋራ ስኬት መሆኑን የጠቆመው አቤል፤ የጉዞ እና የዲጂታል ይዘት ፈጠራ ስራው በተሻለ አቅም እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
