banner

ኤርትራውያን “ሐበሻ” አይደለንም፦ የታሪክ ምሁሩ ዴቪድ ዬህ አዲሱ የምርመራ ጽሑፍ መነጋገሪያ ሆነ

​#FastMereja I የታሪክ ተመራማሪው ዴቪድ ዬህ “ሐበሻ” የሚለው ታሪካዊ መጠሪያ የኤርትራውያንን ብሔራዊ ማንነት ሊወክል ወይም ሊተካ አይችልም ሲሉ ባወጡት አዲስ ጽሑፍ ገለጹ።

​እንደ ዴቪድ ዬህ ማብራሪያ፣ የኤርትራ ብሔራዊ ማንነት በዘጠኙ ብሔረሰቦች (አፋር፣ ብሌን፣ ሒዳረብ/በጃ፣ ኩናማ፣ ናራ፣ ራሻይዳ፣ ሳሆ፣ ትግሬ እና ትግርኛ) ብዝሃነት ላይ የተገነባ እንጂ በአንድ ሰፊ የታሪክ መጠሪያ ስር የሚጠቃለል አይደለም። “ሐበሻ” የሚለው ቃል በታሪክ የጂኦግራፊያዊ አካባቢን የሚያመለክት እንጂ የተወሰነ ብሔርን ወይም አንድን ወጥ ህዝብ የሚገልጽ ባለመሆኑ፣ ይህን መጠሪያ በኤርትራውያን ላይ መጫን የሀገሪቱን ታሪካዊና ፖለቲካዊ ሉአላዊነት ያደበዝዛል ብሏል።

​በጽሑፉ ላይ እንደተመላከተው፣ የኤርትራ ነፃነት ትግል በጋራ ፖለቲካዊ ተሞክሮና በራስ እድልን በራስ የመወሰን መብት ላይ የተመሠረተ የብሔራዊ ነፃነት ተጋድሎ እንጂ በብሔረሰብ ተኮር አስተሳሰብ ላይ የተገነባ አልነበረም። የባህል፣ የምግብ፣ የልብስና የቋንቋ ተቀራራቢነት በአፍሪካ ቀንድ ህዝቦች ዘንድ ያለ ተፈጥሮአዊ ሀቅ ቢሆንም፣ ይህ መመሳሰል የፖለቲካዊ ወይም የብሔራዊ አንድነት ማረጋገጫ ሊሆን እንደማይችል ዴቪድ ዬህ ያሰምሩበታል።

​በተለይም ወጣቱ ትውልድ ባህላዊ ተቀራራቢነትን እና ብሔራዊ ሉአላዊነትን ለይቶ ማወቅ እንዳለበት የጠቆሙት ሪፖርቱ፣ ኤርትራውያን ማንነታቸውን፣ ታሪካቸውን እና ባህላቸውን በራሳቸው ስም “ኤርትራዊ” ብለው መጠራትና ማስከበር እንደሚገባቸው ያሳስባል።

Leave a Comment