banner

6ኛው የአርኪ የሪል ስቴት ኤክስፖ “አዲስ ዓመት አዲስ ቤት” በሚል መሪ ቃል ተከፈተ

​
#FastMereja I አርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ለስድስተኛ ጊዜ የሚያዘጋጀው “6ኛው የአርኪ የሪል ስቴት የቤቶች እና የሱቅ ሽያጭ ኤክስፖ” ዛሬ መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል በታላቅ ድምቀት ተከፈተ። ኤክስፖው እስከ መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን “አዲስ ዓመት አዲስ ቤት” በሚል መሪ ቃል በከተማዋ የሚገኙ የሪል ስቴት ቤቶች እና የሱቅ ገዢዎችን ከሻጮች ጋር የሚያገናኝ ሰፊ መድረክ መሆኑ ተነግሯል።

​የአርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ባለቤት እና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ግርማ ባደረጉት ንግግር፤ ኤክስፖው በዘርፉ ጤናማ የቤት ግብይት እንዲኖር ዓላማ አድርጎ የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም የሪል ስቴት ተቋማት ለደንበኞቻቸው በገቡት ቃል መሠረት ቤቶችን ገንብተው እንዲያስረክቡ ጥሪ አቅርበዋል።

​በተጨማሪም አዘጋጅ ተቋሙ በኤክስፖው ወቅት ለሽያጭ ሠራተኞች የሚሆን ልዩ የማበረታቻ ሽልማት ማዘጋጀቱን አስታውቋል። በዚህም መሠረት የሽያጭ ሠራተኞች ኤክስፖውን የሚያስተዋውቅ ቪዲዮ ሰርተው በቲክቶክ ማህበራዊ ገጽ ላይ በማጋራት 100 እይታ (views) እና 10 ‘ላይክ’ ማግኘት ከቻሉ የ50 ሺህ ብር ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል።





Leave a Comment