banner

ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው ሆነው ከቱርክ ስፔሻሊስቶች የሕክምና አስተያየት የሚያገኙበት ቢሮ ተከፈተ!

#Fastmereja:-በቱርክ በጤና አገልግሎት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑ ተቋማት አንዱ የሆነው አጂባደም ኸልዝኬር ግሩፕ (Acıbadem Healthcare Group) በአዲስ አበባ አዲስ የታካሚዎች መረጃ መስጫ ቢሮ በዛሬዉ እለት ተመርቆ ስራ ጀምሯል።

ይህ ማዕከል፣ አጂባደም በዓለም ዙሪያ ከከፈታቸው ተመሳሳይ ቢሮዎች 52ኛው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ማዕከሉ ኢትዮጵያውያን ታካሚዎችና ቤተሰቦቻቸው ወደ ቱርክ ሳይጓዙ በሀገር ውስጥ ሆነው በአፍ መፈቻ ቋንቋቸው ስለ ሕክምና አማራጮች፣ ስለሚገመቱ ወጪዎችና የጊዜ ሰሌዳዎች ሙሉ መረጃ እንዲያገኙ የሚያስችል ስለመሆኑም ተገልጿል።

በተጨማሪም ማዕከሉ የታካሚዎችን ነባር የህክምና ሰነዶች በመገምገም ከቱርክ ስፔሻሊስቶች ሁለተኛ የሕክምና አስተያየት (second opinion) ማቅረብ፣ የሕክምና ቪዛ እና የጉዞ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣ እንዲሁም ሕክምና ተጠናቆ ወደ ሀገር ከተመለሱ በኋላ የሚደረግ ቀጣይነት ያለው የክትትል አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአጂባደም የአለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ሚስተር ኢሊያስ ቤንቬኒስቴ እንደገለጹት፣ ቢሮው ለአገልግሎት ፈላጊዎች መረጃ ከመስጠት ባለፈ ከኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ጋርበመተባበር የልምድና የእውቀት ሽግግር ለማድረግ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።

በዕለቱ በቦታው የተገኙት ታዋቂው የጉበት ንቅለ-ተከላ እና ሄፓቶቢሊየሪ ቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ፕሮፌሰር አሊ አዘርም ቀደም ሲል በቱርክ ሕክምና አድርገው ከነበሩ ኢትዮጵያውያን ታካሚዎች ጋር የተገናኙ ሲሆን፣ ከሀገር ውስጥ ሀኪሞች ጋርም ቀጣይነት ባለው ሙያዊ ትብብር ዙሪያ ተወያይተዋል።

አጂባደም ኸልዝኬር ግሩፕ በቱርክ፣ ቡልጋሪያ፣ ሰርቢያ፣ ኔዘርላንድስ እና መቄዶንያ 30 ሆስፒታሎችንና 15 የተመላላሽ ክሊኒኮችን የሚያስተዳድር ሲሆን፣ በየዓመቱ ከ50 ሺህ በላይ ዓለም አቀፍ ታካሚዎችን ያስተናግዳል።





Leave a Comment