banner

6ኛው የመልካም ስራ ተምሳሌት ሽልማት የለንደን እና የኢትዮጵያ እጩዎች ይፋ ሆኑ

#FastMereja I በለንደን እና በኢትዮጵያ በጎ ተግባራትን ያከናወኑ፣ በኪነጥበብና በሶሻል ሚድያ የበኩላቸውን አወንታዊ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት የሚሸለሙበት 6ኛው “የመልካም ስራ ተምሳሌት ሽልማት” እጩዎች ይፋ ተደረጉ። እጩዎቹ ይፋ የተደረጉበት መርሃ ግብር እና ጋዜጣዊ መግለጫ ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም. በቦሌ ራማዳ ሆቴል በድምቀት ተካሂዷል።

የመርሃ ግብሩ አዘጋጅ TGS Entertainment ሃላፊ ትዕግስት ንጉሱ በሰጡት መግለጫ መሰረት፣ የዘንድሮው ዋናው የሽልማት ስነ-ስርዓት ህዳር 4 ቀን 2019 ዓ.ም. (ኖቬምበር 14, 2026) በለንደን ከተማ እንደሚካሄድ ታውቋል። በዕለቱ ከእንግሊዝ/ለንደን እና ከኢትዮጵያ የተውጣጡ አርአያነት ያላቸው ሰዎችን የስራ ውጤቶች ለህዝብ ይፋ በማድረግ እውቅና ይሰጥባቸዋል።

እንደ አዘጋጅ ድርጅቱ መግለጫ፣ ከእንግሊዝ/ለንደን ከተመረጡት እጩዎች መካከል ናቲ በቲክቶክ አወንታዊ ኮንቴንት በመስራት፣ ኤፍሬም በዩቲዩብ የፈጠራ ስራዎች፣ ሃና አበበ በአገልግል ሬስቶራንት በጽናት ላሳየችው አገልግሎት፣ እንዲሁም ክራር ኮሌክቲቭ የኢትዮጵያን ባህልና ሙዚቃ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቅ ለሽልማት ታጭተዋል።

በተመሳሳይ ከኢትዮጵያ በኩል እጩ የተደረጉት አካላት ከመቄዶንያ ዶክተር ቢንያም በለጠ፣ በመታሰቢያነት ዶክተር አበበች ጎበና፣ አርቲስት ሄኖክ ወንድሙ፣ እንዲሁም አርቲስት ደሳለኝ ሃይሉ በፊልም ኢንዱስትሪው እና በችግር፣ በድርቅና በጦርነት ወቅት ህዝብንና ወገንን በመደገፍ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ መመረጣቸው ከጋዜጣዊ መግለጫው ለመረዳት ተችሏል።





Leave a Comment