0
#FastMereja I የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር አባል የሆነው ደራሲ ደሳለኝ ግርማ «ምን እግር ጣላት?» በሚል ርዕስ ያሳተመውን ሦስተኛ መጽሐፉን በዛሬው ዕለት ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት አስመርቋል። የመጽሐፉ ምረቃ መርሃ ግብር በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተ መዛግብት አገልግሎት በሚገኘው በመርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ አዳራሽ ተካሂዷል።
በዚሁ በታላቅ ድምቀት በተካሄደው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ታዋቂ ደራስያን፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ጋዜጣኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው ልዩ ልዩ እንግዶች መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝቷል።
የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር አባል የሆነው ደራሲ ደሳለኝ ግርማ ማኅበሩ የሀገራችን ሥነ-ጽሑፍ እንዲያድግና እንዲስፋፋ፣ ደራስያንም በሙያቸው ያላቸውን ችሎታ እንዲያዳብሩ እንዲሁም ድጋፍ ሰጪ አካላት ለጥበቡ እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ማበረታታት ዋና ዓላማው አድርጎ እንደሚሠራ ይታወቃል።




