banner

በሴሬብራል ፓልሲ ለተጎዱ ህፃናት ድምፅ የሆነው ታላቁ የህዝብ እግርጉዞ በዛሬው ዕለት ተካሄደ!

#Fastmereja:- በኢትዮጵያ በሴሬብራል ፓልሲ (CP) ምክንያት ተደራራቢ የአካል ጉዳት ያለባቸውን ህፃናት እና ወላጆቻቸውን በመደገፍ ላይ የሚገኘው «እዝነት አካል ጉዳተኛ ህፃናትና ወላጆች መርጃ ድርጅት» ያዘጋጀው ታላቅ ሀገር አቀፍ የህዝብ እግር ጉዞ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት ተካሄደ።

ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም የሴሬብራል ፓልሲ ቀን አስመልክቶ «ለሲፒ ጉዳተኛ የነገ ተስፋ እጓዛለሁ» በሚል መሪ ቃል የተካሄደው ይህ የእግር ጉዞ፤ መነሻውን ከአዲስ አበባ ፒያሳ ዐድዋ ዜሮ ዜሮ (00) በማድረግ እስከ ኩባ ፓርክ ድረስ ተከናዉኗል።

በዛሬው መርሃ ግብር ላይ የቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔና የዲቦራ ፋውንዴሽን መሥራች አቶ አባዱላ ገመዳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ ባለሀብቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ተማሪዎች እና የአጋር ድርጅት ተወካዮች እንዲሁም የህፃናቱ ወላጆች እና በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በዕለቱ የማርሽ ባንድ፣ የማስኮት (Mascot) ትርኢት፣ የሰርከስ ማሳያ እና የጋራ አካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ከልዩ ልዩ የመድረክ ፕሮግራሞች ጋር ለታዳሚው ቀርበዋል።

የድርጅቱ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዘቢባ አህመድ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት፣ በሴሬብራል ፓልሲ ምክንያት ተደራራቢ ጉዳት የደረሰባቸው ህፃናት ያለ ሰውና መሳሪያ ድጋፍ መቆም፣ መቀመጥና መራመድ የማይችሉ እንዲሁም ስሜታቸውን ከማልቀስ ውጭ መግለጽ የማይችሉ መሆናቸዉን ገልፀዋል።

ወ/ሮ ዘቢባ አክለዉም በርካታ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦችም በድህነት ምክንያት ህፃናቱን ከፀሐይና ከሰው እይታ ሰውረው በቤት ውስጥ ለማቆየት መገደዳቸውን ገልጸው፣ የዛሬው ንቅናቄ ህብረተሰቡ ለነዚህ ህፃናት ድምፅ እንዲሆንና የግንዛቤ እቅቡ እንዲያድግ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት አስረድተዋል።

የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ.ም. የተመሰረተው «እዝነት አካል ጉዳተኛ ህፃናትና ወላጆች መርጃ ድርጅት» በኢትዮጵያ በሲፒ ጉዳተኛ ህፃናት ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ ሁለንተናዊ የድጋፍ ማዕከል በመክፈት ፈርቀዳጅ ሲሆን፣ በማዕከልና በቤት ለቤት ድጋፍ ደረጃ የትራንስፖርት፣ የምግብ፣የመኝታ፣ የንፅህና፣ የፊዚዮቴራፒ እና ለወላጆች የሥራ ዕድል ፈጠራ አገልግሎቶችን ሲሰጥ የቆየ መሆኑ ይታወቃል።





1 comment

Hamud Habibi October 18, 2026 - 1:56 pm

#ወላሂ ለአዚም ከልቤ ነው
በህይወቴ አንድ ነገር ገጠመኝ ልንገራችሁማ ከእለታት አንድ ቀን በሆነ አጋጣሚ የሆነ ችግር ምክንያት ከቢሮ መስሪያቤት በማላውቀው ጉዳይ የስራ እገዳ ይመጣብኛል የታገደድኩም 1 ወር ነገሩ እስኪጣራ ድረስ ተብሎ ከጊዜ በኋላ ቀኑ ደርሶ ነገሮችን ለማጣራት ወደ መስራቤት ስመለስ ነገሮች ወዳልነበሩ ሁነው ነበር ያግኘኋቸው ከስራ እስከመጨረሻው እንደማልመለስ በማስረጃ ተደግፎ ቀረበልኝ በመጨረሻም የማደርገው ሁሉ ጨነቀኝ አንድ የልብ ጎደኛ አለኝ እሱንም ለእሱም ያለውን ነገር ደውየ አማከርኩት በመጨረሻም እንድረጋጋ ነገረኝ ያው እሱም ለኔ ብሎ ከአለበት አገር ድረስ አቋርጦ መጣ ነገሮችን በተለያዩ ነገሮች ለማስተካከል ሞከርን አልሆነም በመጨረሻም ወደ አንድ ቦታ ይዞኝ ሊሄድ አማከረኝ እኔም ያለሁበት ሁኔታ ጨንቆኝ ስለነበር የደስታ ስሜት ተሰማኝ አንድ አባት አሉ ወደ እነሱ ይዞኝ ሄደ ያለውን ችግር ሁሉ ለአባታችን ነገርኳቸው ነገሩ እንዲህ ነው እንደሚያስተካክሉት ነገሩኝ እኔም ማድረግ ያለብኝን ሁሉ አደረኩኝ ከግዚያት በኋላ ከመስራቤታችን ስልክ ተደውሎ እንድገኝ ነገሩኝ እኔም በተባልኩት ቀናት ቀርቤ ምን አዲስ ነገር እንዳለ ሳማክር ወደ ስራየ መመለስ እንዳለብኝ ሲነገረኝ ማመን አቃተኝ ልቤ በደስታ ሞላ ስራዬንም ተመልሼ መስራት ጀመርኩኝ ሲቀጥል ለነዚያ ትልቅ አባት ደውየ ደስታየን አበሰርኩ አይዞህ በርታም ብለው ሌላኛውን እድል እንድሞክር ነገሩኝ የተባልኩትንም የውጭ ፕሮሰስ ሞልቸ ቀናቶችን መጠበቅ ጀመርኩኝ እንደተባለውም ከሁለት ቀን በፊት የሆነ ህልም አሳየኝ እኔም ባየሁት ነገር ተገርሜ ስለነበር መልሼ ወደነዚያ አባት ደወልኩኝ እኔም ያሳየኝን ነገር ነገርኳቸው እሳቸውም ጥሩ ነገር እንደሚገጥመኝ ነገሩኝ እኔም በደስታ ብዛት ልቤ በፍጥነት መምታት ጀመረ ለጓደኛየም ደውየ ስነግረው በጣም ተደሰተ ቀኑም ደርሶ ነገሮችን ለመስማት ጓጉቻለሁ ሆኖም ከቀኑ 5 ሰአት አካባቢ አዲስ የማላውቀው ስልክ ተደወለልኝ ስልኩንም እንዳነሳሁት ደንበኛችን የውጭ ፕሮሰስ በኛ በኩል ሞልተው ነበር አሉኝ አዎ አልኩኝ እንኳን ደስ አለዎት የሞከሩት ፕሮሰስ ተሳክቷል አሉኝ ደስታየ እጥፍ ሆነ ቤቱ በደስታ ሞላ ለዚህም ያበቁኝን አባታችንን ደውየ እንደተሳ ነገርኳቸው እሳቸውም በጣም ደስ እንዳላቸው ነገሩኝ እኔም ለአባታችን የሆነ ነገር አደረኩኝ ፕሮሰሱንም ጨርሼ አሁን በአሜሪካ እየኖርኩ እገኛለሁ ለዚህም ያበቃኝ አላህ ምስጋና ይግባው እኒህንም አባት ለተጨነቃችሁ ለተቸገራችሁ ስልካቸው 🤳 🤳☎️09 47 69 91 95 ነው ደውላችሁ አማክሯቸው የእሳቸው መገኛም ደሴ ውስጥ ይገኛሉ
በimo,በwhatsApp ማግኘት ትችላላችሁ
የሚሠጧቸው አገልግሎቶች፦
➡️ #ለመፍትሄ_ሀብት
➡️ #ለህመም
➡️ #ለመስተፋቅር
➡️ #ቡዳ_ለበላው
➡️ #ለገበያ_ለሁለ_ሰናይ
➡️ #ለመፍትሔ_ስራይ
➡️ #ፍቅረኛ_ላጣ_ወይም_ላጣች
➡️ #ለሎተሪ
➡️ #ለስንፈተ_ወሲብ
➡️ #ድግምት_ለተደገመባችሁ
➡️ #ለእቁብ
➡️ #ለጥይት_መከላከያ_እንዲሁም ሌሎችን ይሰራሉ ☎️09 47 69 91 95
✍️✍️✍️አስተውሉ ከዚህ ውጭ ስልክ የላቸውም
አማክሯቸው እኔን የሰማ አላህ እናተንም ይስማችሁ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Reply

Leave a Comment