banner

በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂና በወጣቶች ማጎልበት ላይ ያተኮረ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ!

#Fastmereja:- በአውቶሞቲቭ እና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለ48 ዓመታት ያገለገሉት ዶክተር አሸናፊ ጸጋዬ፣ በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ዕድገት፣ በግል የሕይወት ተሞክሮ እና በወጣቶች የሙያ ብቃት ላይ የሚያተኩር አዲስ መጽሐፍ አስመርቀው ለንባብ አበቁ።

ከ250 በላይ ገጾች ያሉት ይህ መጽሐፍ፣ የሞተር ቴክኖሎጂ ከቀደሙት የካርቡሬተር ሥርዓቶች ተነስቶ እስከ አሁኑ ዘመን የራሳቸውን የሚያሽከረክሩ (Self-driving) ተሽከርካሪዎች እና የኤአይ አስተዋይነት (AI) ደረጃ የደረሰበትን ታሪካዊና ቴክኒካዊ ጉዞ በሰፊው ይዳስሳል።

የመፅሀፉ ደራሲ ዶ/ር አሸናፊ ፀጋዬ እንደገለፁት የመጽሐፉ ዋና ዓላማ ስኬትን ማብሰር ብቻ ሳይሆን በሕይወትና በሥራ አጋጣሚዎች ያጋጠሙ ፈተናዎችን በማካፈል ወጣቶች ተስፋ ሳይቆርጡ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የራሳቸውን እድል እንዲፈጥሩ ማነሳሳት መሆኑን ገልጸዋል።

ዶ/ር አሸናፊ አክለውም፣ «አሁን ባለው የቴክኖሎጂ ሽግግር ወቅት ወጣቱ ማህበራዊ ሚዲያን ከመጠን በላይ ከመጠቀም ተቆጥቦ የተግባር ልምምድ (Vocational Training) ላይ ማተኮር አለበት» ብለዋል።

በአገራችን እየጨመረ ከመጣው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችና የዘመናዊ ማሽነሪዎች አጠቃቀም አንጻር፣ የወጣቶች በስልጠና መታገዝ ለአገሪቱ የኢንዱስትሪ ዕድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት በምርቃቱ ላይ ተመላክቷል።

መጽሐፉን ወደ አማርኛ ቋንቋ ተረጉሞ ለማቅረብ አራት ወራት ያህል ጊዜ እንደወሰደ የተገለጸ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በገበያ ላይ ለንባብ በቅቶ ይገኛል።





Leave a Comment