banner

ዳቦ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ከዳቦ አምራቾች ጋር መግባባት ላይ ተደረሰ

#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ከአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ የዳቦ አምራቾች ማህበር አመራሮችና አባላት ጋር በዳቦ አቅርቦት፣ ዋጋ እና ጥራት ዙሪያ ተወያይቷል። በተካሄደው የውይይት መድረክ ከ70 ግራም የዳቦ አቅርቦት ጋር ተያይዞ የተካሄደ የዳሰሳ ጥናት ውጤት የቀረበ ሲሆን፣ አምራቾቹ ከስንዴ ዱቄት አቅርቦትና ከብልሹ አሰራር ጋር ተያይዞ ያሉባቸውን ችግሮች ለቢሮው ኃላፊ ለወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ አቅርበዋል።

የንግድ ቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በበኩላቸው፤ የከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰቡን የመግዛት አቅም ያገናዘበ የዳቦ አቅርቦት እንዲኖር ለማስቻል ለዳቦ ፋብሪካዎች ለ10 ዓመታት የሚሆን መሬት በነፃ ከመስጠት ጀምሮ በሸገር ዳቦ በኩል ድጎማ በማድረግ ገበያውን ሲያረጋጋ መቆየቱን ገልፀዋል። አምራቾችም ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን በመወጣት 70 ግራም ዳቦ በብዛትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ማቅረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ በቂ የስንዴ ዱቄት አቅርቦት እንዲኖር በትኩረት እንደሚሰራ የጠቆሙት ወ/ሮ ሀቢባ፤ በአሰራር ላይ የመልካም አስተዳደር ችግር የሚፈጥሩ አካላት ሲያጋጥሙ ህብረተሰቡና አምራቾች በ8588 ነፃ ጥቆማ መስጫ መስመር እንዲጠቁሙና ፈጣን እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል።

በስብሰባው ማጠቃለያም የዳቦ አምራች ማህበራት አመራሮችና አባላት የህብረተሰቡን የመግዛት አቅም ያገናዘበ 70 ግራም ዳቦ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብና ዝርዝሩን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለከተማ አስተዳደሩ ለማሳወቅ የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ከንግድ ቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

4 comments

Fikreab Cachigo October 23, 2026 - 7:29 pm

የተኛውን ዳቦ🤣😂

Reply
Deme Vols Yasin Senayt October 23, 2026 - 7:29 pm

የትኛው ዳቦ ነው ግልፅ አድርገው

Reply
Diriba Fedhasa October 23, 2026 - 7:29 pm

Min🤭

Reply
Astarke Asefa October 23, 2026 - 7:30 pm

Which one 😧

Reply

Leave a Comment