banner

ቴምር ፕሮፐርቲስ በጋርመንት ሳይት የገነባቸውን የንግድ ሱቆች ለባለቤቶቻቸው አስረከበ!

#Fastmereja:- ቴምር ፕሮፐርቲስ በጋርመንት ሳይት ያስገነባቸዉን 56 ዘመናዊ የንግድ ሱቆች በዛሬዉ እለት ለባለቤቶቹ አስረከበ።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የድርጅቱ አመራሮች፣ የንግድ ቤቶቹ ባለቤቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው የእርክክብ መርሃ-ግብሩ የተከናወነው።

የቴምር ፕሮፐርቲስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጃፋር መሀመድ በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ድርጅቱ በገባው ቃል መሰረት ጥራቱን የጠበቀና ለንግድ ምቹ የሆነ ዘመናዊ የንግድ ማዕከል ገንብቶ ለአገልግሎት ማብቃቱን ገልፀዋል።

በ1,498 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ይህ ዘመናዊ ህንፃ ሁለት የከርሰ-ምድር (Basement) ወለሎች፣ የይዞታው ምድር ወለል 19 ሱቆች፣ የመጀመሪያ ወለል 19 ሱቆች እንዲሁም ሁለተኛ ወለል 18 ሱቆችን ጨምሮ በጠቅላላው 56 የንግድ ሱቆችን አካትቶ የተገነባ ስለመሆኑም ነዉ የተገለፀዉ።

ህንፃው ከአፍሪካ ሲዲሲ (Africa CDC) ዋና መስሪያ ቤት እና ከአዲስ አበባ አዳማ ፈጣን መንገድ መግቢያ አካባቢ የሚገኝ በመሆኑ ለንግድና ለኢንቨስትመንት ከፍተኛ አማራጭ እንደሚሆን ተመልክቷል።

ህንፃው ዘመናዊ የሊፍት አገልግሎት፣ አስተማማኝ የመብራት ትራንስፎርመር እና የንፅህና መስመሮች የተገጠሙለት መሆኑም ተገልጻል።

በአጠቃላይ ህንፃዉ 136 የመኖሪያ አፓርትመንቶችን እና 56 የንግድ ሱቆችን በውስጡ የያዘ ሲሆን ለአካባቢው የንግድና የኑሮ ትስስር የበኩሉን አስተዋጽዖ ያበረክታል ተብሎ ይጠበቃል።





Leave a Comment