banner

አርትስ ቴሌቪዥን ከቴክኒካዊ ችግር በኋላ ስርጭቱን በድጋሚ ጀመረ

#FastMereja I በተለያዩ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ምክንያት ለተወሰኑ ቀናት ስርጭቱን አቋርጦ የነበረው አርትስ ቴሌቪዥን ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ ስርጭቱን በድጋሚ መጀመሩን አስታወቀ። ጣቢያው ለተመልካቾቹ ባስተላለፈው ኦፊሴላዊ መልዕክት፣ ስርጭቱ ተቋርጦ በነበረባቸው ቀናት ተመልካቾች ያሳዩትን ፍቅር፣ ድጋፍና ከጎኑ የመቆም ቁርጠኝነት በአክብሮት አመስግኗል።

አርትስ ቴሌቪዥን አያይዞም፤ ከአሁን ጀምሮ የሚወዷቸውን ነባር ፕሮግራሞች ይበልጥ በማጠናከር እና አዳዲስና አጓጊ ይዘቶችን በልዩ ሁኔታ በማዘጋጀት ለአድማጭ ተመልካቾቹ ለማድረስ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል። “የአፍሪካ ህዳሴ ድምፅ” ለመሆን የሰነቀውን ራዕይ አጥብቆ እንደሚቀጥል የገለጸው ጣቢያው፣ ትውልድን በእውቀት የሚያበለጽጉ፣ ማኅበረሰብን በመረጃ የሚያጠናክሩ እንዲሁም የኢትዮጵያን ባህል፣ እሴትና ትውፊቶች የሚያንጸባርቁ ይዘቶችን ማቅረብ የቀጣይ ጉዞው ዋነኛ ተልዕኮ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል።

የጣቢያው አስተዳደር ህብረተሰቡ ከዚህ ቀደም ከጀመረው የትብብርና የድጋፍ ጎዳና ጋር አሁንም አብሮ እንደሚቀጥል ሙሉ እምነት እንዳለው ገልጾ፣ በድጋሚ ወደ ስርጭት መመለሱን በደስታ አብስሯል።

Leave a Comment