banner

በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ አለም አቀፍ የቦክስ ውድድር በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።

አለም አቀፍ የቦክስ ውድድር በኢትዮጵያ አዲስ አበባ “IBA champions night” የተሰኘ ውድድር እንደሚካሄድ ተገለፀ። ዛሬ ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ፣ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን እና የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ እያሱ ወሰን በተገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በIBA champions night ትልልቅ የአለም አቀፍ እና የአፍሪካ ዝነኞች ይጋበዛሉ፣ የአፍሪካ ቦክስ ስራ አስፈፃሚ አባላት እንደሚገኙም ተገልጿል።

ሻምፒዮናው በአዲስ አመት ዋዜማ በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሏል። በአዲስ አበባ የተገነባው የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌደሬሽን ዋና ጽህፈት ቤት እንደሚመረቅም ተነግሯል።

Leave a Comment