banner

በኮድ 2 ተሽከርካሪ ራይድ መጀመሩን ዛይ ራይድ አስታወቀ

ዛይ ራይድ የኮድ 2 መኪኖች ወደ ስራ የማስገባት ፕሮፖዛል በመንግስት ተቀባይነት ማግኘቱን ዛሬ ሐምሌ 13/2016 ዓ.ም የዛይ ራይድ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሐብታሙ ታደሰ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

በአዲስ አበባ የሚታየውን የትራንስፖርት እጥረት ለመቅረፍ ዛይ ራይድ እንደ መፍትሄ የኮድ 2 የቤት መኪኖች በተመጣጣኝ ዋጋ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ እንደሆነ ከአራት ወር በፊት ፕሮፖዛላቸውን ለሚዲያ አቅርበው ነበር። አሁን ፕሮፖዛሉ ተቀባይነት አግኝቶ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን መመዝገብ መጀመራቸውን ገልጿል።

የኮድ 2 ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ 75% ለህብረተሰቡ ቅናሽ ያለው፣ ለአሽከርካሪ ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝ፣ ለመንግስት እስከ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ እንደሚያስገኝ አቶ ሀብታሙ ታደሰ ተናግሯል።

40ሺ መኪኖችን ለመመዝገብ እቅድ እንዳላቸው፣ ምዝገባ መጀመሩን ተገልጿል። የኮድ 2 ባለንብረቶች በምን መልኩ ተመዝግበው ወደ ስራ መግባት እንደሚችሉ፣ ምን ማሟላት እንደሚገባ ተጨማሪ የቪዲዮ ማብራሪያ ተመልከቱ

Leave a Comment