0


አፍሪ ክለብ ኦቨርሲስ ኮንሰልተንሲ ሼር ካምፓኒ ድምፃዊ ቤተልሔም ሸረፈዲንን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ዛሬ ነሃሴ 08/2016 ዓ.ም በሳፋየር አዲስ ሆቴል በተከናወነ ፕሮግራም ሾመ።

ደርጅቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች የዉጭ አገር ስራ ዕድል ፈለጊ ኢትዮጵያዉያን የማማከርና የማሳለጥ አገልግሎት ፣ የዉጭ አገር የትምህርት እድል ማፈላለግ፣ ማማከርና ማሳለጥ ፣ በኦንላይን የዉጭ አገር ቋንቋ ስልጠና መስጠት ፣ የዉጭ አገር የንግድና የምርት ማስተዋወቅ ዝግጅቶች ላይ መሳተፍ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያዉያን ነጋዴዎችና አምራቾች የማማከርና የማሳለጥ ስራዎች መስራት ፣ በዉጭ አገር ህክምና ለሚፈልጉ ኢትዮጵያዉያን ቪዛ የሚያገኙበት ሂደት ማማከርና ማሳለጥ እንዲሁም ኢትዮጵያዉያን ዜጎች የቱሪስት ቪዛ የሚያገኙበትን ሂደት ማማከርና ማሳለጥ እንደሆኑ ተገልጿል።

አፍሪ ክለብ ኦቨርሲስ ኮንሰልተንሲ ሼር ካምፓኒ የሚሰራቸውን ስራዎች ድምፃዊ ቤተልሔም ሸረፈዲን እንድታሰተዋወቅለት ዛሬ የፊርማ ስምምነት አድርገዋል ።