banner

ፈታ ሾው በአባይ ቴሌቪዥን በአዲስ መልክ ሊጀመር ነው ተባለ

የፈታ ሾው ወደ ሚዲያ ሊመለስ እንደሆነ ዛሬ ነሐሴ 9/2016 ዓ.ም በአባይ ቴሌቪዥን ስቱዲዮ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

ከአመታት በኋላ በአዲስ አመት መስከረም 1 በአባይ ቴሌቪዥን ፈታ ሾው “ፈታ ሙዚቃ ሽልማት” የተሰኘ አዲስ ነገር ይዘው መምጣቱን አርቲስት ጌታነህ ፀሐዬ ገልጿል።

በፈታ ሙዚቃ አዋርድ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ያለምንም ቀጥተኛ ውድድር ላበረከቱት አስተዋጾ ለሰራቸው እውቅናን የሚያገኙበት ሁሉን ያካተተ እና አሳታፊ መድረክ ለመፍጠር እንደሆነ ጌታነህ ተናግሯል።

ዝግጅቱ የኢትዮጵያን ባህላዊ እና ዘመናዊ ገፅታዎች ለማንፀባረቅ በትኩረት የታቀደ የሸልማት ትእይንት ብቻ ሳይሆን የባህል አከባበርም ነው ተብሏል።

የፈታ ሙዚቃ አዋርድ ነሀሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በብሄራዊ ቴአትር ሸልማት ሰርዓቱ የሚካሄድ ሲሆን መስከረም 1/2017 ዓ.ም በአባይ ቴሌቪዥን ይተላለፋል።

ፈታ ሙዚቃ አዋርድ በ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያውያን አርቲስቶችን ሰኬት ከማክበር ባለፈ የኢትዮጵያን የሙዚቃ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን እንደያዘ የማክበር እና የመጠበቅን ስርዓት በማስቀጠል የሙዚቃውን ብሎም ሙዚቀኛውን ማስከበር ነው ተብሏል።

ፈታ ሾው “ፈታ በአባይ” በተሰኘ ስያሜ በአዲስ አመት በአባይ ቴሌቪዥን መተላለፍ ይጀምራል።

Leave a Comment