banner

ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሹሟል፡፡ የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ ዙር 3ኛ የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ነው ለርዕሰ መስተዳድሯ ሹመቱን የሰጠው፡፡

አዲስ ሹመት የተከናወነው ወቅቱ የሚጠይቀውን አሻጋሪ የለውጥ አመራር በማምጣት የህዝቡ የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ፍላጎቶች በተገቢው መንገድ ምላሽ እንዲያገኙ ለማስቻል እንዲሁም የቀድሞው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በገዥው ፓርቲ ለሌላ ተልዕኮ በመፈለጋቸው መሆኑም ተገልጿል።

ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ በክልሉ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰ መስተዳድር መሆናቸውም ተገልጿል።

Leave a Comment