ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል ፈጥሮ እየሰራ የሚገኘው ዱባይ ፈርኒቸር በዛሬው ዕለት ቦሌ ማዶ ሆቴል ጀርባ አዲስ በከፈተው ሦስተኛው የመሸጫ ሾሩሙ ውስጥ ከአርቲስት ቃልኪዳን ታምሩ ጋር የብራንድ አምባሳደርነት ፊርማ ተፈራርሟል።
ከተመሰረተ 12 ( አስራ ሁለት ) ዓመት ያስቆጠረው ዱባይ ፈርኒቸር የተለያዩ የቤትና የቢሮ እቃዎችን ከውጪ እንዲሁም ሀገር ውስጥ በማምረት እና በማከፋፈል ምርቶቹን እያቀረበ ይገኛል።
ድርጅቱን የበለጠ ለማስተዋወቅ በማሰብም በተለያዩ ፊልሞች ፣ በቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማዎች እንዲሁም በቴሌብዥን ማስታወቂያዎች ላይ በመተወን የምትታወቀውን አርቲስት ቃልኪዳን ታምሩን የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መርጧል።
የዱባይ ፈርኒቸር ድርጅት ስራ አስኪሀጅ የሆኑት አቶ ጃፋር ሙህዲን እንደገለጹት ” አርቲስት ቃልኪዳን ታምሩ በስነ ምግባሯ እና በሥራዋ ማህበረሰቡ ውስጥ ያላትን ክብር እና ተቀባይነት በመመልከት ብራንድ አምባሳደር እንድትሆን መርጠናታል። ኮንትራቱም ለአንድ ዓመት የሚቆይ ይሆናል” ብለዋል።

ዱባይ ፈርኒቸር የቤትና የቢሮ እቃዎች ንግድ ውስጥ ተሰማርቶ እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነው።
አርቲስት ቃልኪዳን ታምሩ በፊርማ ሥነ ስርአቱ ላይ እንደተናገረችው የዱባይ ፈርኒቸር ብራንድ አምባሳደር ሆና መመረጧ እጅጉን እንዳስደሰታትና ድርጅቱን እና ምርቱን ለማስተዋወቅ እንደምትሰራ ገልፃለች።
አርቲስት ቃልኪዳን ታምሩ ስለክፍያውም ተጠይቃ “መጠኑን መግለፅ ባትፈልግም ጠቀም ያለ ክፍያ እንደተከፈላት ” ገልፃለች ።
ዱባይ ፈርኒቸር አዲስ አበባ ውስጥ ዋና የንግድ መቀመጫውን መስቀል ፍላወር በማድረግ እና ቅርንጫፎቹን ሳህሊተ ምህረት ትራፊክ መብራት አጠገብ እንዲሁም አዲሱ ሾሩሙን ቦሌ ማዶ ሆቴል ጀርባ በውብ ሁኔታ አሰናድቶ በቅርብ ቀን ስራ እንደሚጀምር ገልጻል።