banner

በሰሜን ጎንደር በደረሰ የመሬት መንሸራተት የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ።

#FastMereja
በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ ልዩ ስሙ ኖላ በተባለ ቦታ ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ በሰው ሕይዎት ላይ ጉዳት ደርሷል።

በአደጋው የ10 ሰዎች ሕይዎት አልፏል፣ የአራት ሰዎች አስከሬን በፍለጋ ተገኝቷል ብለዋል። የቀሪ ስድስት ሰዎች አስከሬን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሊገኝ አልቻለም።

በጉዳቱ በስምንት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፣ በመሬት መንሸራተት አደጋው ከ35 በላይ የቤት እንሰሳት ሞተዋል። ከ30 ሄክታር በላይ በሰብል የተሸፈነ መሬት ጉዳት ደርሷል ተብሏል።

በደረሰው አደጋ 480 አባውራዎች እና 2 ሺህ 400 የቤተሰብ አባላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል ሲል አሚኮ ነው የዘገበው።





Leave a Comment