banner

በግፍ ለተገደለው አሸናፊ ደስታ አፋጣኝ ፍትህ እንዲሰጥ ቤተሰብ ጠየቀ።

#FastMereja
ከሁለት ሳምንት በፊት በወላይታ ሶዶ ከተማ ለተከሰተው የግድያ ወንጀል የሚመለከተው አካላት ፈጣን ምላሽ እስካሁን ሊሰጥ አልቻለም ሲሉ ቤተሰብ ቅሬታ አሰማ።

የወላይታ ዞን ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት መምሪያ ሲኒዬር ጂኦሎጅስት አሸናፊ ደስታ በዞኑ የመጠጥ ውሃ ቁፋሮ ስራዎች በማጥናትና የግንባታ ክትትል በማድረግ የህዝቡ ባለውለታ የሆነ ወጣት በድንገተኛ አደጋ ህይወቱ አልፏል።

አሸናፊ ደስታ ታታሪ ፍፁም የሥራ ሰው፣ ቅንና መልካም ሰው እንደነበር የሥራ ባልደረቦቹ ይመሰክራሉ።

አሸናፊ ደስታ ሐምሌ 28/2016 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በሰው ተደብድቦ በጭንቅላት ደም ወደ ውስጥ በማፍሰሱ ምክንያት በክርስቲያን ሆስፒታል ሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ነሐሴ 3/2016 ዓ.ም ሕይወቱ አልፏል።

እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ገዳዮች አልተያዙም ያሉት ቤተሰቦቹ ከግድያው ጀርባ ማን ሊኖር ይችላል የሚለው እስካሁን ያልተመለሰ ጥያቄ ሆኖ ቀጥሏል። ከወጣት አሸናፊ ደስታ ግድያ ጀርባ ስውር እጃቸውን ያስገቡ አካላት በአስቸኳይ ለህግ ይቅረቡም ብሏል።




Leave a Comment