banner

ሦስት ጊዜ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ዳዊት ድሪባ

#FastMereja

በሽብርና በሲቪል አቪየሽን ሕግ ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ተከሶ ዳዊት ድሪባ በዳኔ በሚል ስም ሦስት ጊዜ የሞት ፍርድ የተፈረደበት መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ

በሽብርና በሲቪል አቪየሽን ሕግ ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ ከ1989 ዓ ም ጀምሮ እሰከ 1999 ዓ ም በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ተከሶ ዳዊት ድሪባ በዳኔ በሚል ስም ሦስት ጊዜ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ደጋጋሚ ወንጀለኛ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ታህሳስ 25 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችሎት በዘረፋ፣ በቅሚያ፣ በሌብነት፣ በቤት ሰብሮ ስርቆት እና በደንብ መተላለፍ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ከፖሊስ የምርመራ ማህደር ማረጋገጥ ተችሏል።

ተጠርጣሪው ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ ፣ ጀማል ኑሩ እና ዳዊት ድሪባ በዳኔ የሚሉ ስሞችን በመጠቀም 11 ጦር መሣሪያ መዝረፍ ወንጀል፣ 6 ቅምያ ወንጀል፣ 3 ሌብነት ወንጀሎች፣ 3 ሰው መግደል ወንጀል፣ 2 ስርቆትና ቤት ሰብሮ ስርቆት ወንጀሎች፣ አንድ ሐሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል፣ ከእስር ማምለጥ ወንጀል እና አንድ ደንብ መተላለፍ የወንጀል ሪከርድ በአጠቃላይ 28 የወንጀል ሪካርዶች ያሉበት እንደሆነና ከዚህ ውስጥ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት መጋቢት 24 ቀን በዋለው ችሎት ስድስት መዝገቦችን ሦስት ጊዜ አጣምሮ ሦስት ጊዜ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑን ከፖሊስ የምርመራ ማህደር መገንዘብ ተችሏል።

እንደገና የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ሚያዚያ 30 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችሎት በጦር መሣሪያ የታገዘ የዘረፋ፣ ከአስር ቤት የማምለጥና በሌብነት ወንጀል የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ቅጠት ያስተላለፈት መሆኑን የፖሊስ የምርመራ ማህደር አመላክቷል።

ተጠርጣሪው በውሳኔው መሠረት ማረሚያ ቤት የገባው ይግባኝ ጠይቆ ሞት ፍርዱ ወደ እድሜ ልክ የተቀየረለት ቢሆንም በድጋሚ ይግባኝ በማለቱ ቅጣቱ ወደ 25 ዓመት ተቀንሶለት ለ17 ዓመታት በማረሚያ ቤት ከቆየ በኋላ በይቅርታ መፈታቱን ከፖሊስ የምርመራ ማህደር ማረጋገጥ ተችሏል።

10 comments

Dawit Lemma August 28, 2024 - 6:19 am

በዘመድ ተፈቶ ነው

Reply
የደቡቡ ጥርሰ ብልዝ August 28, 2024 - 6:19 am

እና ሶስቴ ሞቷል ነው ምትሉን🙂

Reply
Umumarya Jm August 28, 2024 - 6:21 am

ምን ይጠበስ

Reply
Senty Negn August 28, 2024 - 6:21 am

ታድያን ይህንን እየሰማንና እያየን ነዉ ሀገር አለን ሀገራችንም መንግስት አላት መንግስትም ህግ አለዉ ፍትህ #ለሄቨን እያልን የምንጮኀዉ🥺

Reply
Yabsira Dejene August 28, 2024 - 6:21 am

በሱ ምክንያተ እነ ጆ ተጠቆሩ በስላሴ መዉጫም የላቸዉ ነገሩ ከብዷል 3ጊዜ የሞተ ነዉ መሀላቸዉ ተይዟል ተበሉ በቃ🤦‍♀️🤦‍♀️

Reply
Dani Yishak August 28, 2024 - 6:22 am

የህግ ሥርአቱ ምን ያህል እንዝላል መሆኑን በደንብ እየነገሩን ነዉ በዚህ አይነት ማረሚያ ቤቱ በፖለቲካ ሠበብ ንፁሀን ነዉ የሚንገላቱበት

Reply
Abinet Petros August 28, 2024 - 6:23 am

ለዚህ አይደል ሕግ ይሻሸል የሚለው

Reply
Anaf Yifru August 28, 2024 - 6:24 am

Besmam mn aynet Hager lay newu yalenewu

Reply
Zoma Mule Zoma Mule August 28, 2024 - 6:29 am

ስንት አመቱ ነው

Reply
Fetene Seyd August 28, 2024 - 6:32 am

ድሮም ያንን የመሰለ ትብብርና ድፍረት ሲያሳዩ ከኋላቸው አንዳች ተልዕኮ እንዳላቸው አያጠራጥርም😎 እንግዲህ ስራቸው ያውጣቸው ከማለት ውጪ

Reply

Leave a Comment