banner

ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በነፃ ጤናማ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሊሰጥ ነው።

#FastMereja
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ፤ አዲስ አበባ ጤና ቢሮ እና ሄኖክ ኪዳነወልድ ስፖርት ስልጠናዎች በመተባበር ለ1000 ሰዎች በውፍረት፣ በኮልሰትሮል፣ በስኳር፣ በደም ግፊት እና በተለያዩ ሱሶች ውስጥ ያሉ የመክፈል አቅም የሌላቸው ሰዎችን በነጻ ስፖርት ለማሰራት የፊርማ ስነ ስርዓት ተከናወነ።

ጤናማ፣ ንቁ፣ ጀግና ዜጋ እንዲሆኑ የማስቻል ዓላማ ያለው ስራ ለመስራት ዝግጅት መጠናቀቁን ዛሬ በካፒታል ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣሚ መግለጫ ተነግሯል።

«ብርቱ ንቁ ጀግና ዜጋ» በሚል መሪ ቃል ከአንድ ሳምንት በኋላ በሚጀመረው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ መውጫ አከባቢዎች በተዘጋጁ የስልጠና ቦታዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ለመሳተፍ በአቅራቢያ በሚገኝ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ተመዝግቦ መሳተፍ እንደሚቻል ተገልጿል። ስልጠናው ለሶስት ወራት የሚቆይ ሲሆን በአመት ሶስቴ ይሰጣል።

ይህ ስልጠና በገንዘብ ሲተመን 30 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ነው ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ልማትና ኢንሸስመንትን በማስፋፋት ስፖርቱ ዓለም የደረሰበት ደረጃ ለማድረስ እና ማሀበረሰቡ በስፖርቱ ጤናውን እየጠበቀ፤ የአንድነት ስሜቱን እየገለፀ የመተጋገዝ ባህሉን እንዲያዳብር ለማስቻል የስፖርት ልማት ስራ እና በጎ ፍቃድ ተግራትን የተለያዩ የስፖርት አደረጃጀቶች በመያዝ በትስስር እየሰራ እንደሆነ ተገልጿል።

📷 FastMereja/ ጥላሁን ደሳለኝ





3 comments

ፍቅር ፍቅር August 31, 2024 - 1:26 pm

አይ ብልፅግና🤔 እስኪ ሰላማችንን ስጡን😏

Reply
Yasin Adim August 31, 2024 - 1:26 pm

በጤፍ ይቀየርልን

Reply
Âbdülhākìm Êyèsūs Krístōs Ãgäpè August 31, 2024 - 1:28 pm

ስፖርት ጥሩ ነው። ነገር ግን
ሰው 👉”ብርቱ ንቁ ጀግና ዜጋ” የሚሆነው 👉 በእየሱስ ክርስቶስ አምኖ የህይወት እንጀራ የሆነውን 👉ወንጌልን ሲያነብ ብቻ ነው ‼️

Reply

Leave a Comment