banner

በጎንደር ወጥተን መግባት፣ በር መክፈት አልቻልንም እገታው አማሮናል አሉ

#FastMereja
“ስለ ጎንደር ዝም አልልም፣ ከተማዬን መልሱልኝ” የተሰኘ ንቅናቄ ተጀመረ።
በአማራ ክልል ጎንደር ወጦ መግባት አልቻልንም በሰቀቀን አልቀናል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ፣ በር ሲንኳኳ እንኳን ለመክፈት ስንቴ ልባችን እንደሚመታ ከተማዋ ላይ ያለው ህዝብ ያውቀዋል፣ ቤተ እምነት ቦታ በፈለግነው ስአት መሄድ አንችልም፣ እናቶቻችን አባቶቻችን ወጠው እስኪገቡ ልጆቼ ምን ሁነው ይሆን በሚል ስጋት በቁማቸው አልቀዋል ሲሉ ያለው መሳቀቅ ነዋሪው ገልጿል።

በጦርነት የተሰቃየችው ከተማ ፣በኑሮ ውድነት መከራዋን የምታይ ከተማ፣ በስራ እጦት ልጆቿ አብረዋት የሚሰቃዩላት ከተማ ይባስ ብሎ አፈናው በቁማችን ገሎናል፣ ድሃ ሀብታም አይልም ለምናችሁ አምጡ ቤታችሁን ሽጣችሁ አምጡ እየተባልን ነው ብለዋል።

ተሳቀን አልቀናል፣ አቅም ያለው ሁሉ ለቋት ሂዷል ሲሉ ነገሩ ከባድ እንደሆነ ተናግሯል።

5 comments

ዙዙ የነቢ September 1, 2024 - 12:50 pm

አልሃምዱሊላህ ህዝቤ ድምጽ ሊያገኝ ነዉ

Reply
Getnet Gashaw Dejenie September 1, 2024 - 12:50 pm

የጎንደር ከተማ ዙሪያ ፋኖዎች ከዓለምሳጋና ደብረታቦር ዙሪያ ካሉ ፋኖዎች ተሞክሮ ይውሰዱ።
ወንበዴን ዝም ጭጭ፣ ፀጥረጭ፣ ጥርግርግ፣ ሙልጭ አድርገውታል።
በድጋሜ ከአምሳሉና ከፀዳሉ ልምድ ይውሰዱ።

Reply
Raggaasaa Abdiisaa September 1, 2024 - 12:50 pm

ወይ ፋኖ የእናንተ ትግል የቄሮ ኮፒፔስት ማረግ ነው አይደለም 😂😂😂

Reply
Esmael Abbaa Jabal September 1, 2024 - 12:50 pm

ለዚህም ፋ * ተጠያቂ ነው ‼️

Reply
Abdi Sona September 1, 2024 - 12:51 pm

ሙስሊሙን ነኩ ማይነካ ቀይ መስመር ነኩ ዛሬ እርስ በእርስ ተባሉ

Reply

Leave a Comment