የቀድሞው የኢዜማ ዋና ጸሀፊ እና የትንሳኤ ሰባ እንደርታ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ኢህአፓን ተቀላቀሉ
እስካለፈው ወር መጨረሻ ድረስ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ዋና ጸሀፊ የነበሩት አቶ አበበ አካሉ እና የትንሳኤ ሰባ እንደርታ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ጊደና መድኅን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲን (ኢህአፓ) ተቀላቀሉ። ሌሎች ሁለት ፖለቲከኞችም ከአንድ ሳምንት በፊት ፓርቲውን መቀላቀላቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል።
ኢዜማ ከተመሰረተበት ከግንቦት 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በዋና ጸሀፊነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ አበበ፤ ከፓርቲው መልቀቃቸውን ያስታወቁት ባለፈው ሐምሌ ወር መጨረሻ ነው። አቶ አበበ ከአዜማ የለቀቁት “ከፓርቲው አቋም እና አካሄድ ጋር ባለመስማማታቸው” እንደሆነ በመልቀቂያ ደብዳቤያቸው ላይ ጠቅሰው ነበር።
አቶ አበበን ጨምሮ አራት ፖለቲከኞች ከ10 ቀን በፊት በይፋ ኢህአፓን መቀላቀላቸውን የፓርቲው የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ መላኩ ካሳ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ይህን በተመለከተ ከ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ አበበ፤ “ምንም ጥርጥር የለውም፤ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ አልወጣም። የምቀላቀልበትን ፓርቲ ግን ጊዜው ሲደርስ እናገራለሁ” ሲሉ በይፋ ከመናገር ተቆጥበዋል።
የቀድሞው የኢዜማ ዋና ጸሀፊ ወደ ኢህአፓ መግባታቸውን ማረጋገጫ ባይሰጡም፤ አቶ አበበ የፓርቲው አባል ለመሆን የሞሉትን ፎርም “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተመልክታለች። የአባልነት ፎርሙ አቶ አበበ ለቀድሞ ፓርቲያቸው መልቀቂያ ባስገቡት ዕለት ኢህአፓን መቀላቀላቸውን ያሳያል። አቶ አበበ ይህን አካሄድ የተከተሉት ኢዜማን በይፋ ሳይሰናበቱ በፊትም ቢሆን ኢህአፓን ለመቀላቀል ያስቡ ስለነበር እንደሆነ የኢህአፓ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አብርሀም ሃይማኖት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስረድተዋል።
ዘገባው የኢትዮጵያ ኢንሳደር ነው።

10 comments
እነዚህማ ሀገርን ይፖሽራሉ ነገ
የክረምቱ የዝውውር መስኮት ሳይዘጋ ዝውውራቸው አጠናቀቁ። ለመሆኑ ዝውውሩ በነፃ ነው ወይስ…?
Here we go
ይቻላል እንደ ለካ 😁
እኔም ልቀላቀል ነዉ😁
ማማሰያ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም😂😂😂
ዝውውሩ ከተከፈተ ሌላ Here we go soon …👍
Here we go Fabrizio Romano ካላለ አናምንም
የአውሮፓ የዝውውር መስኮት እኮ ተዘግቷል በአረብ ሊጉ ነው የተዘዋወሩት😂😂😂
ለ 1 አመት በሚቆይ የውሰት ውል ነው !😂
ማንችስተር ዩናትድንም እንደዚህ አድርጎ ነበረ😂😂