banner

ራይድ ተሸለመ

🌼🌼 በዓመቱ መባቻ አዲስ ስኬት!🌼🌼

የድርጅታችን ዋና ስራ አስፈፃሚ (CEO) ሳምራዊት ፍቅሩ በ2016 ዓ.ም የዓመቱ ስራ ፈጣሪ ዘርፍ ላይ በሕዝብ ምርጫ የ STAR WIDE AWARD ተሸላሚ ሆነዋል::

የ STAR WIDE AWARD ሽልማት በየዓመቱ በተለያዩ ዘርፎች በዓለም ÷ አህጉር አቀፍ እና አገር አቀፍ ደረጃ ላቅ ያለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ እንዲሁም ለማህበረሰባቸው ጥራት ያላውና አስተማማኝ የሆነ አገልግሎት ላበረከቱ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የሚበረከት ልዩ ሽልማት ነው::

ራይድ ትራንስፖርትም በሥራ ፈጠራው ዘርፍ እንደሀገር ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይህ ታላቅ ሽልማት ተበርክቶለታል :: እንደሚታወቀው ራይድ ትራንስፖርት በአሁኑ ሰአት ከ76 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች ጋር የፓርትርሺፕ ውል በመዋዋል በከተማው በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ለዚህም አስፈላጊውን የቢሮ ፋሲሊቲ በማሟላትም በስሩ 500 የሚሆኑ ሰራተኛችን በመያዝ ስራውን እያከናወነ ሲሆን÷ በከተማው ከፍተኛ የሆነ የስራ እድል በመፍጠር ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት በማቅረብ ከፍተኛ ሚና እየተጫተ መሆኑ እሙን ነው፡፡

ራይድ ትራንስፖርት በአገር አቀፍ ደረጃ ከፈጠረው ከፍተኛ የስራ እድል በተጨማሪ ስራውን ሲያከናውን ፈጣን ፣ደህንነቱ የተጠበቀ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት በመስጠት የከተማውን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ ረገድም የድርሻውን ሲወጣ ቆይቷል፣ በቀጣይም ለከተማችን ነዋሪዎች ስላምና ደህንነት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በቁርጠኝነት ይሰራል፡፡

ውድ የከተማችን ነዋሪዎች ለዚህ ታላቅ ሽልማት እንድንበቃ ስለመረጣችሁን ምስጋናችን የላቅ ነው፡ ሽልማቱ ነገን በላቀ ትጋትና ጥራት እንድናገለግላችሁ ብርታት ይሆነናል፡፡ ራይድ ሁሌም አገልግሎቱን የበለጠ በማዘመን ተደራሽ ÷ ብቁ እና ተወዳዳሪ እንዲሁም አስተማማኝ አገልግሎት አቅራቢ እንዲሆን የናንተ የውድ ድንበኞቹ ድጋፍ ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል እና ሽልማቱ የናንተም ነው ::

መጪውን ዓመት በራይድ አብረን እንጓዝ!
🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት 🌼🌼

##RIDE8294 #📞 8294

http://Bit.ly/2GrFBNz


Leave a Comment