ሀገራችንን ለመውረር ግፊት ሲያደርጉና ግጭት ሲያባብሱ የነበሩ የሀገራችን ታሪካዊ ጠላቶች አብረው የቆሙ ቢመስሉም በሽንፈት ጊዜ እንደማይገናኙ ከታሪክ መማር ይገባል !!
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በ47ኛው የምስራቅ ዕዝ ምስረታ በዓል ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም
👉 የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ከሰላም ወዳዱ የሱማሌ ህዝብና ከጀግናው የዕዙ አመራርና አባላት ጋር ለማክበር በመቻሌ ደስታ ተሰምቶኛል፤
👉 ዕዙ አንደኛ አብዮታዊ በሚል ስያሜ የዛሬ 47 ዓመት መመስረቱና ከምስረታው ማግስት ጀምሮ ተስፋፊውን የዚያድ ባሬ ጦር ጨምሮ የተለያዩ የሽብር ሀይሎችን በመከላከልና በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተሰጠውን ግዳጅ በጀግንነት ሲመክት የቆየ አንጋፋና ጀግና ዕዝ መሆኑን፤
👉 ዕዙ ተስፋፊውን የዚያድ ባሬ ጦር ወደ መሀል ሀገር ያደረገውን ወረራ መስዋዕትነት በመክፈል ጭምር የሀገሩን ዳር ድንበር ማስከበር መቻሉን፤
👉 በክልሉ ለታየው ሰላምና እየተመዘገበ ላለው ሁለገብ እድገት የተረጋገጠው ሰላም ወሳኝ በመሆኑ ክልሉ ለልማትና ለኑሮ ተመራጭ እየሆነ መምጣቱን፤
👉 ዕዙ የሀገራችን ሰላም ሉአላዊነትና አንድነትን በማስጠበቅ ከፍተኛ ዋጋ መክፈሉና የሰራዊቱ መመኪያ የሆነ ዕዝ መሆኑን፤
👉 ክልሉ በፀጥታ ችግር ምክንያት ከልማት ርቆ መቆየቱና ዕዙ መንግስትና ህዝቡ ባስመዘገቡት ሰላም በፈጣን ሁኔታ ዕድገቱ እያደገ መምጣቱን፤
👉 ተስፋፊነት የጦርነት ነጋሪት መሆኑንና ሠራዊታችን ሀገራችንን ለመውረር የሞከሩ ሀይሎች ለመመከት የሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ፤
👉 ሀገራችንን ለመውረር ግፊት ሲያደርጉና ግጭት ሲያባብሱ የነበሩ የሀገራችን ታሪካዊ ጠላቶች አብረው የቆሙ ቢመስሉም በሽንፈት ጊዜ እንደማይገኙ ከታሪክ መማር እንደሚገባ፤
👉 ሠራዊቱ በቀጠናው ያለውን የተስፋፊዎች የጦርነት ነጋሪት ጉሸማ ለመመከት የሚያስችል የተሟላ ወታደራዊ ቁመና ላይ እንደሚገኝና ህዝባችን ላይ ስጋት ለመፍጠር የሚሞክሩ ተላላኪዎችን መስማት እንደሌለበት፤
👉 ውስጣዊ ችግሮች ቢኖሩም ሀገርን ከጥቃት ለመከላከል ብቻ ሳይሆን ከሞከሩ ዳግመኛ እንዳያስቡት አድርጎ ለመመከት የሚያስችል ዝግጁነት መኖሩን የተናገሩት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፤
የሀገራችንን ነፃነት አስከብረን እንኳን አሁን በጦርና በጋሻ ታንክ በመመከት በነፃነት የቆየን የጀግኖች መገኛ መሆናችንን የምስራቁ የሀገራችንን ድንበር ለመመከት ለዕዙ የሚደረግ ማንኛውንም ድጋፍ መከላከያ እንደሚያደርግ መላው የሀገራችንና የክልሉ ማህበረሰብ ለዕዙና ለሰራዊታችን የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩን ቀጥሏል።





3 comments
Always Ethiopia 😘❤❤❤
Yejeginoch midre genet
ይህን 👉😂 react የምታደርጉ ባንዶች ለምን ተሰብስባችሁ ወደምትወዱት አገራችሁ ግብፅ አትሄዱልንም? እኔ ፈጣሪዬን ሁሌም የማመሰግነው እነዚህ ኢትዮጵያ እትዮጵያ እያሉ ሲያደነቁሩን ኖሮ ዛሬ የለመዱት ጥቅማቸዉ የቀረባቸዉ ሲመስላቸዉ አገርን ክዶ በባንዳነት ተሰልፈዉ ለግብፅ ሲያሽቃብጡ በማየቴ ነዉ። ለካስ ባንዳነት ከዘር ነዉ።