ዕድገቱ በዛብህ ለፋስት መረጃ ከዳውሮ ታርጫ
በቶኪ በኣ ዕለት በዳውሮ አካባቢ ሰው ሁሉ ቤት ያፈራውን ጠግቦ በልቶ የሚያድርበት፣ ከብቶች ሣር ጠግበው በልተው የሚያድሩበት፣ እንዲሁም በቤት ውስጥ ያለ ባዶ ማድጋ በውሃ፣ በወተትና በማር እንዲሁም በተለያዩ ባህላዊ መጠጦች ተሞልተው የሚያድርበት የጥጋብና የሙላት ምሳሌ የሆነ በዓል ነው።
በቶኪ በኣ የተጣሉ የሚታረቁበት፣ ዘመድ አዝማድ ተሰብስቦ በመጪው አመት እቅድ ላይ የሚመክሩበት፣ በጋራ ማዕድ የሚቋደሱበት የአንድነትና የአብሮነት ምሳሌ የሆነ የብሔሩ ባሀላዊ ዕሴት ሲሆን ይህም መጪው ዘመን የጥጋብ፣ የፍቅርና የይቅርታ እንዲሁም የመተሳሰብ እንዲሆን የመልካም ምኞት መግለጫ ነው።
በዳውሮ ዞን በርካታ ቅርሶች ያሉት ሲሆን የቀደምት ዳውሮ አባቶች የስልጣኔ ማሳያ የኾነው የካቲ ሀላላ ኬላ፣ በአለም ርዝመቱ አቻ ያልተገኘለት ረዥሙ የእስትንፋስ ሙዚቃ መሳሪያ ድንካ፣ የጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ እንዲሁም የሀላላ ኬላ ቅንጩ ሎጂ ይገኙበታል።
ዳውሮ የባህል ጭፈራዎች፣ የአመጋገብ ስርዓት፣ የጋብቻና የለቅሶ ስነስርዓት እንዲሁም ዛሬ በድምቀት የተከበረው ቶኪ በኣ “Layitsa Laamiya” ያለው ሲሆን የባህል ምግቦቹ ኡታ፣ ስልሶና ሱልሶ፣ ባጭራና ብራቶ፣ ሲልሶና ታንጮ… በርካታ ናቸው።
በዘንድሮው የቶኪ በኣ በዓል ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በዓሉን ለመታደም ታርጫ ከተማ የተገኙ የብሔሩ ተወላጆች ጋር በዳውሮ ቋንቋና ባህል ሲምፖዚየምም በትናንትናው ዕለት አካሂደዋል።
“Yiiya layitsay Loome” መጪው ዘመን እንደ ሎሚ መልካም ሽታ ያለው ይሁን ማለት ነው።
መልካም የቶኪ በኣ በዓል!





6 comments
እናመሰግናለን Fast mereja
እናመሠግናለን
መልካም በዓል💐❤
Robinho Danna Danna እንኳን አደረሰህ
❤❤❤
አከባበሩን እንዴት እንየው ይሄ ሰውዬ አያለ።