banner

ብራና ሆቴል በሜቄዶንያ አባቶች ተመረቆ ተከፈተ !

#FastMereja
ብራና ባር እና ሬስቶራንት በሚል ስያሜ ከዚህ ቀደም 22 በሚገኘው ዘሪሁን ህንጻ አካባቢ ተከፍቶ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ወደ ሆቴል ደረጃ ከፍ ብሎ ሁለተኛውን ቅርንጫፉን 22 በሚገኘው ባታ ኮምኘሌክስ ህንጻ ላይ በዛሬው እለት ከሜቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በመጡ አረጋዊያን አባቶች በተገኙበት በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል።

ብራና ሆቴል ዘመናዊና ከፍተኛ ኢንቨስትመንት በጠየቁ ግብአቶች የተደራጀ እና የተሟላ አገልግሎትን የሚሰጡ 30 የመኝታ ክፍሎች ፤ ካፌ እና በጣፋጭ ምግቦቹ የሚታወቀው ሬስቶራንት፣ ሌሎች አገልግሎቶችን ለመስጠት መዘጋጀቱን የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ታምራት ገብሬ ገልፀዋል።

ሆቴሉ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ባሻገር በማኀበራዊ ስራዎች ላይ በንቃት እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን ዛሬን ጨምሮ ላለፉት ሁለት ቀናት ለአካባቢው ማህበረሰብ የነጻ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ አቶ ታምራት ገብሬ ጨምረው ገልጸዋል።

ዝግጅቱን ያስተባበረው Adina Events & Promotion ነው ::





Leave a Comment