banner

አድማስ ዩኒቨርሲቲ 16ኛውን ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ጉባኤ አካሄደ

#FastMereja
አድማስ ዩኒቨርስቲ 16ኛውን ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ጉባኤ አካሄደ። ዛሬ ጳጉሜ 2/2016 ዓ.ም የተለያዩ የዩኒቨርስቲው አመራሮች በተገኙበት በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል አካሄዷል፡፡

የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ሞላ ጸጋ (ዶ/ር) እንደገለጹት ባለፏት 14 ዓመታት ዩኒቨርስቲያቸው የትምህርት ጥራቱን ማዕከል ያደረገና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ጉባኤ ሲያካሂድ መቆየቱን አስታውሰው በዚህ ረገድ ሃላፊነታቸውን ሲወጡ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርስቲው ለዘንድሮው ጉባኤ የመረጠው የጥናትና ምርምር ርዕስ “የከፍተኛ ትምህርት ጥራት፣ ጥናትና ምርምር እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎት በኢትዮጵያና በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ” የተሰኘ ሲሆን ለአንድ ሀገር ወሳኝ የሆነውን የትምህርት ጥራትና ከዩኒቨርስቲዎች ተልዕኮ አንዱና ዋነኛው የሆነውን የማህበረሰብ አገልግሎት ከኢትዮጵያ አልፎ አፍሪካ ቀንድን የሚዳስስ የጥናትና ምርምር ወረቀት በጉባኤው ቀርቧል።

በዘንድሮውም የጥናትና ምርምር ጉባኤ ከላይ በተመረጠው ርዕስ ዙሪያ ምሁራን ጥናትና ምርምር ስራቸውን እንዲያቀርቡ በመጋበዝና ከቀረቡት ውስጥ የተሻለ ይዘት ያላቸውን በማወዳደር በዛሬው እለት ለጉባኤው ማቅረባቸውን የገለጹት ሞላ ፀጋ (ዶ/ር) በዚህም ዘርፍ እየታየ ያለውን ክፍተት ለመሙላት መፍትሄ ጠቋሚ የሆኑ የጥናትና ምርምር ውጤቶች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

በዚህ ጉባኤ ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና ከባለ ድርሻ አካላት የተወከሉ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።





Leave a Comment