#FastMereja
ታዋቂዋና ተወዳጇ የቴሌቪዥን ሾው አቅራቢ ዳናዊት መክብብ ከኢቢ የስ ፈርኒቸር ጋር በብራንድ አምባሳደርነት ድርጅቱ የሚያመርታቸውን እና የሚያስመጣቸውን ምርቶች ለማስተዋወቅ ዛሬ ጳግሜ 4 /2016 ዓ.ም በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ በከፍተኛ ክፍያ መፈራረሟ ተገለፀ።
የድርጅቱ ተወካይ የሆኑት አቶ ሄኖክ ብርሀኑ በስነ ስርአቱ ላይ እንደገለፁት ኢቢ የስ ፈርኒቸር ለ 10 ዓመታት የተለያዩ ጥራት ያላቸው የቢሮና የቤት እቃዎችን በከተማችን ለሚገኙ ትላልቅ የመንግስት እና የግል ድርጅቶች በማቅረብ ተመራጭ የሆነ ድርጅት ነው:: በአዲሱ 2017 ዓመትም እጅግ ምቹ እና ውብ የሆኑ አዳዲስ የቤት እና የቢሮ ፈርኒቸር ምርቶችን በሃገር ውስጥ በማምረት እና ከውጪ በማስመጣት የደንበኞቹ እርካታ እና የምርቶቹን ጥራትን የበለጠ ከፍ ለማድረግ ማቀዱን ተወካዩ አሳውቀዋል ፡፡
ከዳናዊት ጋር ለመስራት በመወሰናቸው የተሰማቸውን ደስታ የገለፁ ሲሆን በህዝብ ዘንድ ያላትን ተቀባይነት እና ተወዳጅነት በመጠቀም የኢቢ የስ ፈርኒቸር ምርቶች ለደንበኞቹ እንደምታስተዋውቅ ገልፀዋል::
ተወዳጇም የቴሌቪዥን ሾው አቅራቢ ዳናዊት መክብብም ከኢቢ የስ ፈርኒቸር ጋር አብራ በመስራቷ የተሰማትን ደስታ ገልፃለች:: ለዘመነ የኑሮ ዘይቤ ኢቢ የስ ፈርኒቸርን ይምረጡ በማለት መልዕክቷን ከማስተላለፍ በተጨማሪም መጪው አዲስ አመት መልካም የስራ ዘመን እንዲሆን ምኞቷን አስተላልፋለች፡፡




10 comments
🤔🤔🤔
የሰራተኞቹን ደሞዝ ቢጨምር አይሻለውም ነበር 👎👎👎
EBS ሳጢያ ብለህ የነገርከን ልጅ የት ነህ?
ተሳስታ ቃና ውስጤ ነው እንዳትል
ዳቦዋን ሸጣ አለፈላት
ቆያ ወንድ አሆንም እንደ
ተወዳጅ ያደረጋት ማነው? ጋጠወጥ ስነምግባር የሌላት ለሌላው አርዐያ መሆን የማትችል ነች
ይሄን አለባበስ ለዚ ፕሮግራም ብላ ከሰው ተውሳ እንጂ የለበሰችው የሱዋ አለባበስማ …
ላለው ይጨመራል
ሴቶች አለባበሳችሁ ሁሌም እንደዚህ በሆነ🤔🙄