#FastMereja
በትግራይ ክልል የቃላሚኖ ልዩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪው ዮናስ ንጉሰ በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 675 በማምጣት በደረጃው የምንጊዜውንም ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል፡፡
በተመሳሳይ ተማሪ ሔለን በርኸ ከቃላሚኖ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 662 በማምጣት ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡት ተማሪዎች መካከል አንዷ ናት፡፡
ዮናስ ንጉሰ እና ሔለን ባለፉት ዓመታት ያጋጠሟቸ ሁለት ፈተናዎች ኮቪድ-19 እና የሰሜኑ ጦርነት በትምህርታቸው ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድሮ ማለፉን ይናገራሉ፡፡
በእነዚያ ጊዜያት የባከነውን ጊዜያቸውን በውጤት ለመካስ ጠንክሮ መስራትን መምረጣቸውን ነው የገለጹት፡፡
በቃላሚኖ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2016 ዓ.ም ለፈተና ከተቀመጡ 282 ተማሪዎች መካከል በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛው ውጤት የተመዘገበው በተማሪ ዮናስ ንጉስ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የተማሪ ዮናስ ውጤትም እስካሁን ከነበሩት ውጤቶች ሁሉ ከፍተኛ መሆኑን ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት፡፡
ሽረ እንደስላሴ ተወልዶ ያደገው ተማሪ ዮናስ ትምህርት ከየትኛውም ጫና ነፃ መሆን እንዳለበት እና በትምህርት ላይ የሚደርሰው ጉዳት እንደሀገር ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑን ገልጿል፡፡
በተመሳሳይ ተማሪ ሔለን በርኸ ከቃላሚኖ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 662 በማስመዝገብ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች መካከል አንዷ ናት፡፡
ለዚህ ውጤት መመዝገብ የቃላሚኖ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያደረገላቸው እገዛ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚወስድ ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
ተማሪዎቹ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ባስመዘገቡት ውጤት መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

10 comments
ድሮም መነፅር ምያረግ ሰዉ አደገኛ ነዉ
ትግራይ 💪💪💪🤙🤙🤙💛❤️💛❤️💛 🤓🤓
የምንጊዜም ማለት ምን ማለት ነው
በጣም ይገርማል ከ3 አመት ከባድ ጦርነት ምንም ሳይበገሩ ትልቅ ውጤት ማምጣታቸው..#proud of you tegarus❤
የምንጊዜም ማለት ግን አይከብድም
የምንግዜም ማለት ምን ማለት ነው?
እንኳን ደስ አላችሁ ከነቤተሰቦቻቸው
ሁለቱም መነፅር አድርገ
ዋል
የትግርኛ ስሞች ሳትቀይሩ መፃፋችሁ ጥሩ ጅምር ነው።
ከፍተኛና በጣም ደስ የሚል ዉጤት ነው:: “የምንጊዜም ከፍተኛ ” ???