banner

እስከ ሞት ቅጣት ተወስኖባቸው የነበሩ 178 የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በይቅርታ እንዲለቀቁ ተወሰነ

በትግራይ ጦርነት ወቅት “የተሰጣቸውን ህገ- መንግስታዊ ተልዕኮ ወደ ጎን በመተው በሰራዊቱ እና በህዝብ ጥቅሞች ላይ ወንጀል በመፈጸም” እስከ ሞት ቅጣት ተወስኖባቸው ለነበሩ 178 የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ይቅርታ መደረጉን መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

እንደ መከላከያ ሠራዊት መረጃ ይቅርታ የተደረገላቸው የሠራዊት አባላቱ፤ በጦረነቱ ወቅት ፈጸመዋል በተባለው ወንጀል በወታደራዊ ፍትህ ስርዓቱ አማካኝነት ክስ ተመስርቶባቸው በወታደራዊ ፍርድ ቤቶች እስከ ሞት ቅጣት ተወስኖባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙ ናቸው።

የሠራዊት አባላቱ “በፈፀሙት ወንጀል ተፀፅተው የይቅርታ ጥያቄአቸውን ለመንግስት እና ለመከላከያ ሚኒስቴር ማስገባቻወን” ያስታወቀው መከላከያ ሠራዊት፤ በአንድ በኩል ጉዳያቸው ለይቅርታ ቦርድ ቀርቦ በአዋጅ ቁጥር 840/2006 አንቀፅ 3 ድንጋጌ መሰረት ይቅርታ ማድረግ የሚያሳካቸውን አላማዎች ግምት ውስጥ በማስገባት እና እነዚህ የሰራዊት አባላት በፈፀሙት ወንጀል መፀፀታቸውም ተመልክቷል ብሏል።

የመከላከያ ሚኒስቴር የይቅርታ ቦርዱን ውሳኔ መሰረት በማድረግ በመታረም ላይ የነበሩ 178 የሠራዊት አባላት ከዛሬ ጳጉሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከእስር በይቅርታ እንዲለቀቁ መወሰኑን አስታውቋል ሲል አዲስ ስታንዳርድ ነው የዘገበው።

10 comments

Fasil Kehali September 10, 2024 - 10:24 am

ግብፅ !!

Reply
Abebe Degefe September 10, 2024 - 10:26 am

ለዝህ እኮ ነው ሀገርቷ ለይ ህገ ወጥነት የበዘው መንም ወንጀል ይሠራል ነጌ በይቅርታ

Reply
Mamayo Anayo September 10, 2024 - 10:27 am

የእኛ ወታደሮች እንደ ዶሮ እንድታረዱ ምክንያት የሆኑ እና አደገኛ ኦፕሬሽን ስራውቱ ላይ የፈፅሙ በመሆናቸው ይቅርታ በፍፁም አያስፈልጋቸውም።
እቃወማለሁኝ።

Reply
አዲሱ ወንድሙ አደሜ September 10, 2024 - 10:28 am

ብዙ የምምር ብዙ ይማራል!!

Reply
Bayu Bayu September 10, 2024 - 10:33 am

የሞተ ተጎዳ

Reply
Tesfaye Tayera September 10, 2024 - 10:41 am

ወክለን ያልጠበቀ እዉነቱን ያላገናዘበ ዉሳኔ!

Reply
Misikir Art September 10, 2024 - 10:51 am

እናንተ ለስልጣናችሁ አስጨርሳችሁ ታረቃችሁ። አለቀ

Reply
Desalegn D. Dangura September 10, 2024 - 10:53 am

የድሃው ኢትዮጵያዊው ልጅ በእነሱ ሴራ እንደ በግ አንገቱ የታረደውና ጡታቸው በቁም የተቆረጡ ሴት ጓድቶቻችን ደም ላይ የሚቀልድ መንግስት እንጂ ደም የሚመልስ እንደለለ በሚገባ እየተረዳን ነው!ግድ የለውም ለሁሉም ነገር ፈጣሪ አንድ ቀን ፍርድ ይሠጣል።

Reply
Evad A. Zemoy September 10, 2024 - 10:56 am

ትግራዋይ በመሆናቸዉ ብቻ ነበር የታሰሩት !

Reply
Bam Daily September 10, 2024 - 11:02 am

በትግራዋይነታቸዉ ነበር የታሰሩት👐
እንኳን የታጠቀ ሰራዊት ማንም ስቪል ትግራዋይኮ ያለሃጥያቱ ሲታጎር ነበር ።

Reply

Leave a Comment