banner

ቴክኖ ሞባይል የአዲስ አመት መዳራሻን ምክንያት በማድረግ በማሪዎት ሆቴል አይቪ ላውንጅ በተዘጋጀ የማስተዋወቂያ እና የኢትዮጵያ

ቴክኖ ሞባይል የአዲስ አመት መዳራሻን ምክንያት በማድረግ በማሪዎት ሆቴል አይቪ ላውንጅ በተዘጋጀ የማስተዋወቂያ እና የኢትዮጵያ አዲስ አመት ፕሮግራም ሶስት አዳዲስ የቴክኖ ሞባይሎችን ማለትም የቴክኖ ፋንተም ቪ2 ፍሊፕ እና ፎልድ ታጣፊ ስልኮችን እና ቴክኖ ካሞን 30 ኤስ ፕሮ ሞዴሎችን ለተጠቃሚው አስተዋውቋል፡፡ በተጨማሪም የቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ ብራንድ አምባሳደር ከሆነቸው ዳናይት መክብብ ጋር ያለውን የስራ ኮንትራት አራዝሟል፡፡

አዲሱ የቴክኖ ፋንተም ቪ 2 ፍሊፕ ስልክ ወደ ታች የሚታጠፍ የ5G ኔትወርክ ማስጠቀም የሚያስችል እና እጅግ ዘመናዊ ሆኖ የተሰራ ስልክ ሲሆን ካለፈው ቪ1 ሞዴሉ በካሜራው በፊት እና በኋላ ስክሪኖቹ እንዲሁም በባትሪ አቅሙ ተሻሽሎ ቀርቧል፡፡

የቴክኖ ፋንተም ቪ 2 ፎልድ ስልክ በበኩሉ የ5 ጂ ኔትወርክን ማስጠቀም ከማስቻሉ ባሻገር ወደ ጎን የሚታጠፍ እና የተለያዩ ስራዎችን በአንድ ጊዜ መከወን የሚያስችል እንዲሁም የቢዝነስ ስራ ላይ ለተሰማሩ እንዲሁም ለመዝናኛ ስልኩን መጠቀም ለሚፈልጉ እና ለሌሎችም ስራዎች እጅግ ምቹ ተደርጎ ተሰርቷል፡፡

የቴክኖ ካሞን 30 ኤስ ፕሮ በበኩሉ የካሞን 30 ተከታይ ሞዴል ሲሆን ከፍ ያለ አቅም እና ቴክኖሎጂን፣ ካሜራን እንዲሁም ከርቭድ ስክሪንን አካቶ መቷል፡፡

በፕሮግራሙ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ አርቲስቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ የሚዲያ ባለሙያዎች ፣ የቴክኖ ሞባይል ሃላፊዎች እና የቴክኖሎጂ አድናቂዎች የተገኙ ሲሆን ተጋባዥ እንግዶቹ ስልኮቹን በቅርበት የመመልከት ዕድል እንዲኖራቸውም ሁሉም አዳዲስ ሞዴሎች ለዕይታ ቀርበዋል፡፡





Leave a Comment