❓
የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና ልዑካን ከስድስት ቀናት የዋሽንግተን ዲሲ ቆይታ በኋላ ትናንት ሌሊት ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ጀምረዋል፤ በአሜሪካ የቀሩ ተጫዋቾችና የቡድን አባላት ግን አሉ፥ እነሆ፦
🟡 ቅዱስ ጊዮርጊስ
👉 ከተጫዋች
አማኑኤል እንዳለ…የቀኝ መስመር ተከላካይ
አሸናፊ ሞሼ….የቀኝ መስመር ተከላካይ
ቢንያም እንዳለ…. ተከላካይ
አቢሴሎም ዘመንፈስ…አማካይ
👉 ከህክምና ቡድን
ሙሉነህ ቤካ… ፊዚዮትራፒስት
👉 ከህዝብ ግንኙነት
ካሳሁን ደርበው…የክለቡ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ
ቸርአምላክ ሀብተማርያም…የክለቡ ቪዲዮ ተንታኝ
ከቅዱስ ጊዮርጊስ አጠቃላይ አሜሪካ የቀሩ ብዛት….7️⃣
🟤 ኢትዮጵያ ቡና
➡️ ከተጫዋች
ሱራፌል ሰይፈ…አማካይ
ቃልአብ ፈለቀ…አማካይ
ኪያር መሀመድ…ቀኝ መስመር ተከላካይ
➡️ ከህክምና ቡድን
ሰለሞን ሀይለማርያም…ፊዚዮትራፒስት
➡️ ከህዝብ ግንኙነት
ዮሀንስ እድሉ…የህዝብ ግንኙነት
★ከኢትዮጵያ ቡና አሜሪካ የቀሩ ብዛት…5️⃣
★በአጠቃላይ እስካሁን ከሁለቱም ቡድኖች 1️⃣2️⃣ ልዑካን አሜሪካ ቀርተዋል
🔔 ተጨማሪ መረጃዎች
✔️ የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ ከቡድኑ ጋር ወደ አዲስ አበባ አልሄደም፤ የመመለሻ ትኬቱ ወደ አርብ ተቀይሮለታል
✔️ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሀኪም ዶ/ር ተስፋማርያም መኩሪያ በተመሳሳይ ከቡድኑ ጋር አልተመለሱም
✔️ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አማካይ ያብስራ ተስፋዬና የኢትዮጵያ ቡናው ግብጠባቂ እስራኤል መስፍን ስማቸው ከመቅረት ጋር ቢያያዝም ከቡድኑ ጋር ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል
✔️ በእሁዱ ጨዋታ ከሁለቱም ቡድኖች በመልማዮች አይን ውስጥ የገቡ ተጫዋቾች ሲኖሩ ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ አሜሪካዊ ዜግነት ያለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ አማካይ ሊያስፈርም ተስማምቷል
✔️ በወዳጅነት ጨዋታው ያሸነፈው ኢትዮጵያ ቡና ለተጫዋቾቹ ለእያንዳንዳቸው 100ሺህ ብር ሸልሟል
★ በመጨረሻም የአዲስ አመት ዋዜማ የሙዚቃ ግብዣ
ጋባዥ፦ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱት
ተጋባዥ፦ አሜሪካ የቀሩት
ድምፃዊ፦ ግርማ ነጋሽ
የመጀመሪያው ስንኝ..
“ምነው ተለየሽኝ መስከረም ሳይጠባ፣
እንቁጣጣሽ እያልን ሳናጌጥ በአበባ”
(በታምሩ ዓለሙ)

2 comments
እንኳን ጠፎ ለየትኝው ኳሳቸው ነው
መንግስታችን ራሱ ሸም ይዞት እንጅ መጥፋት ይፈልጋል ከኢትዮጵያ