banner

ሲቢኢ ብር ፕላስ የእንቁጣጣሽ ኤክስፖ የ2.5 ሚሊዮን ብር የኤሌክትሪክ መኪና በመሸለም ተጠናቀቀ።

#FastMereja
ሲቢኢ ብር ፕላስ የእንቁጣጣሽ ኤክስፖ ተጠናቀቀ። ኤክስፖ ከፍተኛ ጎብኚ እንዳገኘ ተነግሯል። ለ21 ቀናት ሲካሄድ የነበረው ኤክስፖ ትናንት ጷጉሜ 5/2016 ዓ.ም በአዲስ ዓመት ዋዜማ የተጠናቀቀ ሲሆን ሊጠናቀቅ በመጨረሻው ቀናቶች በቀን እስከ 25ሺህ ብር ጎብኚ ድረስ እንደመጣ ተገልጿል።

በመጨረሻው እለት 2.5 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ቢዋይዲ የኤሌክትሪክ መኪና እና የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ለአሸናፊዎች ሽልማት ተበርክቷል።

ሲቢኢ ብር ፕላስ የእንቁጣጣሽ ኤክስፖ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ታይትል ስፖንሰርነት በታሜሶል ኮሙኒኬሽን እና ከአሴንቲክ ሶሉሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።

ታሜሶል ኮሙኒኬሽን ኢግዚቢሽን ማዕከል የገበያ ልማት ኢንተርፕራይዝ ያወጣውን ጨረታ በ62 ሚሊዮን ብር በማሸነፍ የእንቁጣጣሽ 2017 የአዲስ አመት ኤክስፖ ሲያካሂድ ቆይቷል።

“ሲቢኢ ብር ኘላስ ኤክስፖ 2017″ ከሸመታና ከጉብኝት በተጨማሪ በየቀኑ ከ35 በላይ ተወዳጅ ድምጻዊያን ያቀነቀኑበት ሲሆን የሙዚቃና የመዝናኛ ፌስቲቫልም በአጋፔ ኢቨንት በኩል ተዘጋጆ ቀርቧል።

📷 FastMereja





2 comments

Kete Strike Frist September 11, 2024 - 11:31 am

ጉድ ነው የት ነው ይሄ ነገር

Reply
Kalu Ayaliew September 11, 2024 - 11:59 am

ተው ባክህ ወሬ

Reply

Leave a Comment