በጉጂ ዞን በሻኪሶ ከተማ አስተዳደር ለቅርጫ ስጋ ለመከፋፋል በሚል የታሰረውን በሬ ሰርቆ ለመሸጥ የሞከረው ግለሰብ ላይ የቅጣት ውሳኔ መተላለፉ ተገልጿል።
የሻኪሶ ከተማ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ሻምቦ ፊቶ እንደገለጹት ኦዶ ሻኪሶ ቀበሌ ላይ ተከሳሽ ብርሃኑ ሮባ የተባለው ግለሰብ ለአዲስ ዓመት የተዘጋጀው በሬ ፈቶ በመውሰድ ወደ ገበያ በማምጣት ለመሸጥ ሲሞክር በቁጥጥር ስር መዋሉን በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
ግለሰቡ በሬውን ሻኪሶ ከተማ በንቱ የተባለ የገበያ ስፍራ በመውሰድ በአርባ ሺህ ብር ለመሸጥ ሲሞክር የበሬው ባለቤት አቶ ኡርጋ ባደሮ የጠፋውን በሬ ገበያ ውስጥ በማየታቸው ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉ ተጠቁሟል።
ፖሊስ በሬውን እና ግለሰቡን በቁጥጥር ስር በማዋል በአስቸኳይ የምርመራ መዝገቡን በማጣራት ለዓቃቢ ህግ የላከ ሲሆን ዓቃቢ ህግ ጉዳዩ በፈጣን ችሎት በመመልከት ለወረዳው ፍርድ ቤት መዝገቡን አቅርቧል።
መዝገቡን የተመለከተው የኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ፍርድ ቤት ጷግሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ብርሃኑ ሮባ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ3 ዓመት ከሰባት ወር እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑን ኢንስፔክተር ሻምቦ ፊቶ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

3 comments
ይብላው
Waggawu 😄 🤣
ደሞ በመታሰሩ የተከፋ እይመስልም😁
ፈገግታው ገዳይ ነው😂