banner

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትግርኛ ቋንቋ እና የፍልስፍና ትምህርቶችን ተማሪ በማጣቱ ዘጋ

#FastMereja

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ18 ዓመት በፊት የተቋቋመውን የትግርኛ ቋንቋ እና ስነ ጹሁፍ ትምህርት ክፍልን፤ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ሊዘጋ ነው። በፍልስፍና ትምህርት ክፍል በመጀመሪያ ዲግሪ የሚሰጠው ትምህርትም፤ ከዚህ ዓመት ጀምሮ እንዲቋረጥ ዩኒቨርስቲው ውሳኔ አስተላልፏል።

አንጋፋው ዩኒቨርሲቲ ከእዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው፤ የትምህርት ክፍሎቹ ላለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት አዲስ ተማሪዎችን ባለመቀበላቸው ነው።

“ትግርኛ ለምን ተማሪ እንዳጣ ዋናው ምክንያት የታወቀ ነው። በጦርነቱ ምክንያት ነው። እሱ ጎድቶናል። ተማሪው በየት አድርጎ ይምጣ” ሲሉ የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ አቶ ሀድጉ ተካ የችግሩን ምክንያት አስረድተዋል። የትግርኛ ቋንቋ፣ ስነ ጹሁፍ እና ፎክሎር ትምህርት ክፍል አዲስ ተማሪዎችን ለመጨረሻ ጊዜ የተቀበለው በ2010 ዓ.ም ነበር።

እንደ ትግርኛ እና ቋንቋ ስነ ጽሁፍ ሁሉ በተመሳሳይ ምክንያት እንዲቋረጥ በዩኒቨርሲቲው ውሳኔ የተላለፈበት ሌላው የትምህርት አይነት፤ በመጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ የሚሰጠው የፍልስፍና ትምህርት ነው። የፍልስፍና ትምህርት ክፍል ከ2011 ዓ.ም ወዲህ በመጀመሪያ ዲግሪ መርሀ ግብር አዲስ ተማሪዎችን አለመቀበሉን የትምህርት ክፍሉ ኃላፊው ዶ/ር ፋሲል መራዊ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ዘገባው የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው።

10 comments

Estifanos Gudeta September 14, 2024 - 11:48 am

The Eviction of Addis residents from their homes is CRIME AGAINST HUMANITY!!!!!
#justiceforwellegagenocideinethippia

Reply
Sur Sur September 14, 2024 - 11:48 am

ማስተማር ስላልፈለገ።

Reply
ዳንኤል ደሳለኝ September 14, 2024 - 11:49 am

ወደፊት ተማሪ በማጣቱ ሙሉ ለሙሉ ተዘጋም ይባል ይሆናል😉

Reply
Yaekob Getahun September 14, 2024 - 11:50 am

ፍልስፍና የማይማር ትዉልድ ፈጠራችሁ በዚሀ አጭር ዕድሜ 😁😁 ትምህርት እየገደላችሁ ነዉ እነ ብሬክስ እና ሳሙኤል (ዶ/ር)። ዝም ብሎ የሚነዳ ትዉልድ በመፍጠር ትዉልድ ያስታዉሳቿል። ማሰላሰል ቀረ!

Reply
Tesfaye Mehari September 14, 2024 - 11:50 am

ጥሩ ነዉ ሲጀመር አስፈላጊም አልነበረም ።

Reply
Jemal Smn September 14, 2024 - 11:51 am

እንደውም አስመራ ዩኒቨርስቲ ይቀርበናል።

Reply
Jõhññy Dëssãlegñ September 14, 2024 - 11:53 am

የብርሃኑ ነጋ እጅ አለበት

Reply
Kalkidan Dawit September 14, 2024 - 11:53 am

አይደል፣ ተው እንጅ፣ ምነው ፎለቲካ የማይገባን መሀይማን ነው እንዴ የምንመስላችሁ

Reply
Kibru Doge September 14, 2024 - 11:53 am

የደብረፅዮን እና የጌታቸው የፍጥጫ ውጤት🤝🤗

Reply
Ashu Ja September 14, 2024 - 11:53 am

መንግስት ከተለያዩ አገራት ጋር ገብቶ በአገሪቱ ሃብት በድሮን ገደላቸው እኮ ። ከየት መጥቶ የማሩ

Reply

Leave a Comment