የሊቨርፑል ኮከብ ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ የፈረንሳዩን ክለብ FC Nantes (ኖንት) ለመግዛት ” 84ሚ.ፓ የጨረታ ዋጋ አቅርቧል”::
#FastMereja
ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ የፈረንሳዩን ክለብ ለመጠቅለል ንግግር እያደረገ እንደሆነ ከወደ ፈረንሳይ የሚወጣ ሀተታ ዘግቧል::ጉዳዩ ይጠናቀቅ/ይፈጸም እንደሆነ እንመለከታለን…
አሌክሳንደር አርኖልድ ክለቡን ለመግዛት ጠይቋል በእርሱ በኩል ፈቃዱንም ገልጿል::
የ25 ዓመቱ የሊቨርፑል ተከላካይ በቅርቡ በዝውውር ጉዳይ ስሙ በስፋት ከሪያል ማድሪድ ጋር ተያይዞ ነበር በክለቡ ያለው ውል በቀጣይ ዓመት ሊጠናቀቅ መሆኑን ተከትሎ:: እናም በክለቡ የወደፊት ቆይታው ዕቅድ ላይ ብዙ ትኩረት ነበር::
አሁን ግን እንግሊዛዊው ኖንትን ከመግዛት ጋር ተያይዞ በክለብ ባለቤትነት ሂደት ውስጥ ብቅ ብሏል::
አሁን ላይ ክለቡ በባለቤትነት የተያዘው በፈረንሳዊው ነጋዴ Waldermar Kita (ቫልደርማር ኪታ) ስር ነው::
ከ L’Equipe (ሊ’ኪፕ) የተገኘው አዲሱ ሀተታ እንደሚለው አሌክሳንደር አርኖልድ እና አባቱ ሚካኤል በቅርቡ ከክለቡ ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው ከማውራታቸው አስቀድሞም በርቀት ለጥቂት ጊዜያት ተወያይተዋል::
አሌክሳንደር አርኖልድ ለንደን ውስጥ በአባቱ የሚተዳደር የንግድ ድርጅት/ኩባንያ አለው:: አሁን መግዛት ለፈለገው ክለብ መነሻ 100ሚ.ዩሮ (84ሚ.ፓ) 80ሚ.ዩሮ ቀድሞ የሚከፈል 20ሚ.ዩሮ በሗላ:: በተጨማሪም 40ሚ.ዩሮ የገንዘብ ጉርሻ ያለው::
በሁለቱ አካላት መካከል (በክለብ ሻጭ እና ገዢ) ሀሙስ ዕለት ለንደን ውስጥ ስብሰባ/ውይይት ተደርጎ ነበር:: ነገር ግን ያቀረቡት ገንዝብ (የእኛ የሚሉት የገንዘብ ይዞታ) ከአሁኑ የክለቡ ባለቤት ኪታ የዋጋ ግምት ጋር አልተገናኘም::
ይሄ ወሬ መሰማቱን በኖንት የክለቡ ሹም አልወደዱትም አበሳጭቷቸዋል:: ዘገባውንም እያስተባበሉ ነው::
አሌክሳንደር አርኖልድ ይህንን ክለብ ለመግዛት መርጦ ዋጋ ከማቅረቡ በፊት ሌሎች ክለቦችንም ተመልክቷል እዚያው ፈረንሳይ Saint-Etienne (ሰንቲ-ቲዬን)እና Le Havre (ል አቭኸ)
ተከላካዩ አስቀድሞ ከፍሬንች ፎርሙላ ዋን ቡድን Alpine (አልፒን) ጥቂት ድርሻ አለው::
[ሰላም ጎሳዬ በፋስት መረጃ ከአዲስ አበባ ኢትዮጵያ]


10 comments
ብርታት እና ጥረቱ… ገንዘብ አያያዙ በዚህ እድሜው በጣም ይገርማል 👏👏👏 ይጣራልን ይጣራልን ይሄማ ስር መሠረቱ ጉራጌ ነው 😀
የእንግሊዙ ጉራጌ 😂
yene Arnold ❤
በቅርበት ለመከታተል ሊቨርፑል ,ዩናይትድ ወይም አርሰናልን ብገዛ ይሻለዋል
መረጃው የጎደለው ነገር አለ
ከሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው ያቀረበው
Collab አርጎ ነው መረጃ ይስተካከል ምገዛው team እኮ ሀምበሪቾ አደለም
እዛም የ ደብተራው ነገር አለ ማለት ነው🤭
ሊቨርፑል አሌካዝንድሮ መልቀቅ ብዙ ዋጋ ያስከፍለዋል ባይ ነኝ።
በቃ ተሰፋ የለወም ሊቨርፑል ክለበ
መጀመሪያም ይሄ ልጅ የጉራጌ ዝርያ አለበት ብዬ ነበር ቋጣሪ 😁