banner

አዳብና የልጃገረዶችና ወንድ ወጣቶች ጨዋታ መተጫጫ ፌስቲቫል በክስታኔ በድምቀት ይከበራል።

#FastMereja
አዳብና የልጃገረዶችና ወንድ ወጣቶች ጨዋታ መተጫጫ ፌስቲቫል ከመስከረም 16 እስከ ጥቅምት 5 በክስታኔ ቤተ- ጉራጌ በድምቀት እንደሚከበር አዳብና በከስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር ዛሬ መስከረም 10/2017 ዓ.ም በቶቶት የባህል አዳራሽ በሰጡት መግለጫ አስታውቋል።

የአዳብና ባህል የልጃገረዶችና ወጣት ወንዶች ጨዋታና መተጫጫ ስነስርዓት ሲሆን ባህሉ በጥናት በተረጋገጠ መረጃ መሰረት 800 ዓመታት በፊት በክስታኔ ቤተ-ጉራጌ አካባቢ ለዘመናት ሲከበር ኖሯል።

ይህ ባህል በተለያዩ ምክንያቶች ደብዝዞና ሊጠፋ ተቃርቦ የነበረ ሲሆን የአዳብና በከስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር ከአካባቢው የመንግስት መዋቅሮች ጋር በመሆን ባደረገው ጥረት ባህሉ ጥንታዊ ወጉና ቱባ ባህሉ ይዞ በከፍተኛ ሁኔታ በማንሰራራት በአሁን ሰዓት በአካባቢው ላይ በፌስቲቫልነት እየተከበረ ይገኛል።

አዳብና በክስታኔ ጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ከጫወታ ባለፈ ወጣቶች የሚተጫጩበትና ትዳር የሚመሰርቱበት የወጣቶች ባህል ነው። ይህም በአካባቢው ዘንድ ትዳር የሚመሰረተው በሁለቱ ታቃራኒ ፆታ ምርጫና መፈቃቀድ ብቻ የነበረና የሴቶች መብትና ነፃነት የተጠበቀ መሆኑን ያሳያል።

አዳብና በከስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር ይህ ድንቅ የሆነ የአዳብና ባህል በሀገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ በፌሲቲቫልነት እንዲታወቅና በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት በUNESCO እንዲመዘገብ እንዲሁም የቱሪስት መስህብ በመሆን ለአካባቢውም ለአገራችን ኢትዮጵያም የገቢ ምንጭ እንዲሆን አዳብናን የማስተዋወቅ ስራዎች እየሰራ ነው።

በያዝነው 2017 ዓ.ም ማህበሩ የአዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር አዳብናን ሰፋ ባለና በደመቀ ሁኔታ በፌሲቲቫልነት ለማክበር ከፍተኛ ዝግጅቶች ያደረገ ሲሆን ዘንድሮ ፌሲቲቫሉ በምስራቅ ጉራጌ ዞን መስከረም 18 ኬላ ከተማና በሌሎች የሶዶ-ከስታኔ አካባቢዎች የሚከበር ይሆናል።

📷 FastMereja / ጥላሁን ደሳለኝ





Leave a Comment