banner

በመዲናዋ ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ የትራንስፖርት አገልግሎቱን ለማሳለጥ እንቅፋት የሚሆኑ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይ

በመዲናዋ ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ የትራንስፖርት አገልግሎቱን ለማሳለጥ እንቅፋት የሚሆኑ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠርና የአቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ብቻ በተመረጡ መስመሮች ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ ቢሮው ገልጿል፡፡

መስመሮቹም ከቦሌ – ፒያሳ፣ ከቦሌ – ሜክሲኮ፣ ከቦሌ – አራት ኪሎ፣ ከቦሌ – አውቶቢስ ተራ፣ ከቦሌ – ሽሮሜዳ፣ ከጀሞ – ፒያሳ እና ከጀሞ – ሜክሲኮ ሲሆኑ በተመሳሳይ ከፒያሳ – ቦሌ፣ ከሜክሲኮ – ቦሌ፣ ከአራት ኪሎ – ቦሌ፣ ከአውቶቡስ ተራ – ቦሌ፣ ከሽሮ ሜዳ – ቦሌ፣ ከፒያሳ ጀሞ፣ ከሜክሲኮ – ጀሞ ከመጪው እሁድ መስከረም 12/2017 ዓ.ም ጀምሮ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ብቻ መሰጠት ይጀመራል፡፡

የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩ አንደኛ የመንገድ መዘጋጋቱን ለመቀነስ፤ ሁለተኛ ብዙ የሰው ቁጥር ያለው ተጓዥ በአንድ ጊዜ ለማመላለስ፤ በዚህም ተማሪና መምህራን ብሎም ሌሎች ተገልጋዮች በሰዓታቸው ወደ ሚፈልጉት ቦታ በመንቀሳቀስ አገልግሎት እንዲያገኙ ያግዛል ብሎም በከተማዋ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው የተነቃቃ እንዲሆን እንደሚረዳም ቢሮው አስታውቋል፡፡

ስለሆነም በመዲናችን የምትገኙ ነዋሪዎች ይህንን አውቃችሁ በተለይ ህብረተሰቡ የብዙሃን ትራንስፖርትን የመጠቀም ልምዱን እንዲያጎለብት እና ለትራንስፖርት አገልግሎት መሻሻል የሚከናወኑ ተግባራትን በማገዝ የሚጠበቅበትን የዜግነት ግዴታ ጭምር እንዲወጣ ቢሮው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

በዚህ ረገድ በማንኛውም እንቅስቃሴ ወቅት የትራንስፖርት አገልግሎት በምታገኙበት ጊዜ የሚያጋጥማችሁንና በሚስተዋሉ ችግሮች ዙሪያ በአካል በቅርበት ለሚገኙ የትራንስፖርት ቁጥጥር ሰራተኞች እንድታሳውቁ ወይም በ9417 በነፃ የስልክ ጥሪ መስመር እየደወላችሁ ጥቆማ እንድትሰጡም ጭምር ቢሮው አስታውቋል፡፡

መረጃው፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

3 comments

የዑራኤል ልጅ ነኝ September 20, 2024 - 10:51 am

በቃ አዲስ አበባ ላይ ከቦሌ እስከ 4 ኪሎ ፒያሳ ብቻ ነው እሚታያችሁ? በየሰፈሩ ስንት የትራንስፖርት ችግር እንዳለ ማን ይንገራችሁ?

Reply
Firaafis Diinaafis September 20, 2024 - 10:53 am

ግልፅ አይደለም ምን ማለት ነው?

Reply
Axum Tsion September 20, 2024 - 10:54 am

የገባው ያስረዳኝ

Reply

Leave a Comment