የንግድ ትርኢት ኤግዚብሽንና ባዛር በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ተከፈተ
በዞኑ ወልቂጤ ከተማ የተከፈተው የንግድ ትርኢትና ባዛር የከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲነቃቃና ገጽታዋ እንዲጎላ ከማድረግ ባለፈ የህብረተሰቡን እሴት በማስተዋወቅ ረገድ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን የጉራጌ ዞን አስተዳደር ገለጸ።
የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ እንዳሉት የንግድ ትርኢትና ባዛር መዘጋጀቱ የከተማው የንግድ እንቅስቃሴ ከማሳለጥ ባለፈ የህብረተሰቡን ባህልና እሴት በማስተዋወቅ ረገድ ፋይዳው ትልቅ ነው።
በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ባዛርና ኤግዚብሽን የሚዘጋጅ መሆኑን ያነሱት አስተዳዳሪው በከተማዋ የተዘጋጀው የንግድ ትርኢትና ባዛር በጥራት፣ በመጠንና በዋጋ ተወዳዳሪና ተመራጭ እንዲሆን መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
የንግድ ትርኢትና ባዛሩ በሰላማዊ መንገድ እስኪጠናቀቅ ድረስ የዞኑ አስተዳደር አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግ አቶ አበራ ገልጸዋል።
ተግባሩ እንዲሳካ ላደረጉ ለዞንና ከተማ አስተዳደር የንግድና ገበያ ልማትና ለባህል ቱሪዝም ተቋማት እንዲሁም ለአዲና ኢቨንት እና ፕሮሞሽንና ለሎችም ምስጋና አቅርበዋል።
የባዛሩ መዘጋጀት ማህበረሰቡ የሚፈልጋቸው እቃዎች በአንድ ማዕከል እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገር በዋጋ ደረጃ ቅናሽ እንዳለው አቶ መላኩ አንስተዋል።
በንግድ ባዛርና ኤግዚብሽኑ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን ይህም ማህበራዊ ትስስርና መስተጋብሩን የበለጠ እንደሚያሳልጥ ገልጸዋል።
የአዶት የጉራጌ ዞን የነጋዴ ሴቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ሮዛ አግዛ ማህበሩ በነጋዴው ማህበረሰብን እና በመንግስት መካከል እንደ ድልድይ በመሆን በአሁኑ ወቅት የሚስተዋለውን ህገወጥ ንግድ፣ ሰው ሰራሽ የዋጋ ንረት፣ ከካፒታል በላይ ክምችቶችን በተቀናጀ መንገድ በመግታት ጉልህ አበርክቶ ያደርጋል ብለዋል።
ዘገባው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።





1 comment
Good