banner

ነገዎ ጂማ የ4 ሚሊዮን ብር መኪና ተበረከተለት።

#FastMereja
ረጅሙ ኢትዮጵያዊ ወጣት ነገዎ ጅማ ከኦክሎክ ሞተርስ መኪና ተበረከተለት። ዛሬ መስከረም 09/2017 ዓ.ም በድርጅቱ ቅጥር ግቢ በተካሄደ ፕሮግራም ላይ Wuling የተሰኘ 8 ሰው መጫን የሚችል የ4 ሚሊዮን ብር መኪና ተበርክቶለታል።

የኦክሎክ ሞተርስ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ አህመዲን መሐመድ ባደረጉት ንግግር “ነገዎ በሰይፉ ሾው ላይ ቀርቦ ያደረገውን ንግግር ተመልክቻለሁ ተመልሶ ይቅርታ በማለቱ ለይቅርታ ልቡ የተሰጠው ስጦታ ነው። በዚህ መኪና ስራ እየሰራ ራሱን እንዲያስተዳደር አበርክተንለታል።» ብለዋል።

ነገዎ ጅማ ለተሰጠው መኪና በጣም ደስተኛ መሆኑን እና ያልጠበቀው ስጦታ መሆኑን ገልጾ ኦክሎክ ሞተርን ለስጦታው አመስግኗል።

በኦክሎክ ሞተርስ በርካታ መኪናዎች የሚገኙ ሲሆን ከፍሎ መውሰድ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው መኪናዎቹን መረከብ እንደሚችል ተገልጿል።





2 comments

Abebayehu Geta Enaro September 19, 2024 - 2:07 pm

እሰይ ከዚህች ሀገር ከመውጣት ታደግነው👍

Reply
ሙፉቲ ነኝ ፀረ ዲን September 19, 2024 - 2:08 pm

መርሀባ

Reply

Leave a Comment