0
#FastMereja
የስምምነቱ ዋና ዓላማ ሁለቱ ተቋማት የክፍያ አገልግሎቶችን ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በቀላሉ እና በአነስተኛ ወጪ ማድረስ ላይ በጋራ ለመስራት ነዉ፡፡
ኦሮሚያ ባንክ በሀገራችን እየጨመረ የመጣዉን የፍይናንስ ቴክኖሎጂ ፍላጎት ከግምት ዉስጥ በማስገባት ዘመኑ የሚፈልጋቸዉን አዳዲስ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶችን ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለደንበኞቹ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡
ቻፓ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ ሀገር በቀል ድርጅት ሲሆን ከዚህ ቀደም የገንዘብ ቴክኖሎጂዎችን፣ ሰው ሠራሽ አስተዉሎት (አርተፊሻል ኢንተለጀንስ) በመጠቀም የፋይናንስ ስርዓቱን ለማዘመን እየሰራ ይገኛል።
ኦሮሚያ ባንክ የፋይናንስ እንቅስቃሴዉን ከማሳለጡ በተጨማሪ ለሀገራችን የፋይናንስ ዲጂታላይዜሽን በማዘመን የራሱን አስተዋዕፆ እያበረከተ ይገኛል፡፡
📷 FastMereja / ጥላሁን ደሳለኝ





1 comment
ቻፓ የሚለዉ ቃል በተለይም በምስራቁ የሀገራችን ክፍል አዳማን ጨምር ማህተብ ለማለት የሚጠቀሙት ቃል ነዉ ወደ መሀል ሀገር ደግሞ ሌላ ትርጓሜ ነዉ ያለዉ