0
አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ/ማ ከብልህ ማርኬቲንግ ጋር በቀጣይ 90ቀናት የሚተገበር ካምፔንን በማስመልከት በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ።
መስከረም 21/2017 ዓ.ም
የፊርማ መርሀ-ግብሩ ስነ-ስርዐት ቦሌ በሚገኘው የአሸዋ ቴክኖሎጂ ዋና መስሪያ ቤት የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት ተከናውኗል፡፡
የአሸዋ ቴክኖሎጂ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ የERP(የተቋማትን አሰራር የሚያዘምን የጊዜ፣የገንዘብ፣የሰው ሀይል ብክነትን የሚቀንስ) እና የNehabi (ዌብሳይት ለመገንባት ምቹ እና ቀልጣፋ ፈጣን) በተለያዩ አክቲቪቲዎች ለዌብሳይት አበልፃጊዎች እንዲሁ ለተለያዩ ተቋማት ችግርን የሚፈታ አሰራርን የሚያዘምን ይበልጥ ቀልጣፋ የሚያደርገውን ምርቶችን ለአገልግሎት ፈላጊዎች ለማድረስ የሚያግዙ ስትራቴጂዎችን በመቅረፅ በቀጣይ 3ወራት የሚተገበር BTLን በጋራ ለመስራት በዛሬው እለት የተፈራረሙ መሆኑ ታውቋል።
በቅርቡም ሚድያዎችን በመጋበዝ ዝርዝር መግልጫ የሚሰጥ መሆኑን ማወቅ ተችሏል።




